ሰላም ቤተሰብ እንዴት ናችሁ 👋🏽 የመንግስት ሰራተኛ ነኝ እና ድሮ ሱስ ነበረብኝ። ክብርና ምስጋና ለራሴ ይሁንና አሁን ነፃ ነኝ። እና ምን ላማክራችሁ መሰላችሁ ከባለፈው አመት ጀምሮ ከመልበስ እና ከመብላት ሚተርፈኝን ብር ማስቀመጥ ጀመርኩ እና አሁን 46,000 ብር ደርሷል። ዝም ብዬ አስቀምጣለሁ እንጂ ጎል የለኝም እና አሁን ማሰብ ጀመርኩ ለምንድነው ማጠራቅመው ብዬ ራሴን ስጠይቅ ምንም መልስ የለኝም። ምን ትመክሩኛላችሁ። አሁን ባለኝ ብር ልጀምረው ምችለው በትርፍ ሰዓት ሚሰራ ቢዝነስ ካለ ጠቁሙኝ። 24 አመቴ ነው ተንቀሳቅሼ በደንብ መስራት እችላለሁ እና አዲስ አበባ ነው ምኖረው። ከ10 ሰአት በኋላ እና እሁድና ቅዳሜ ነፃ ነኝ። አመሰግናለሁ 🙏
May 09, 2022እሺ ወንድማችን እራስህን ከሱስ አላቀህ ከወጪ ቀሪ 46000 ብር መቆጠብህ በእውነቱ በጣም ነው የሚያስመሰግንህ ወደ ገደለው ስንገባ መጀሪያ 1, መንጃ ፍቃድ ከሌለህ ህዝብ አንድ አውጣ 2,የትምህርት ደረጃህን ዲፕሎም ከሆንክ ወደ ዲግሪ ዲግሪ ከሆንክ ወደ ማስትሬት አሳድግ 3, በትርፍ ሰአትህ የሞባይል ካርድ ለሱቆች እና ለሱቅ በደረቴዎች በቅናሽ ዋጋ አከፋፍል 4, አንድ 30000 ብር ከቤተሰብ ወይ ከጓደኛ እንደምንም ተበድረህ በ 80000 ብር ትንሽዬ ጫማቤት ነገር ክፈት 5, በእለት የሚጣል በቀን የ1500 ብር እቁብ ግባና በአንድ ወር ውስጥ 150000 ብር ተቀብለህ አሪፍ ቢዝነስ ጀምር 6 , ነጋዴ ጓደኛ ካለህ አንተ በብርህ እሱ ትርፍ ለጋራ ስሩ 7, 8, 9. 10, 7,8,9,10 ሌላ ጊዜ እንመካከርበታለን
May 10, 2022