ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁንና ይህ ቃል ምን ማለት እንደሆነ ስንመለከት ከላይ ስለአገልጋይ በምሳሌ ሲናገር ቆይቶ በመጨረሻ ይሄን ያለው ለምንድን ነው ብለን ለመረዳት ስንሞክር ሐዋርያትን እናንተ በ12 ዙፋን ላይ ተቀምጣችሁ በዚህ ህዝብ ላይ ትፈርዳላችሁ። (ሉቃ 22:29-30) ያለውን ወደአእምሮአችን እናምጣና እረዷቸው ሲል ግደሏቸው ነው ነገር ግን ከአገዳደል ሁሉ የከፋ አሟሟት መሆኑን እረዷቸው በማለቱ ይታወቃል። የሰው ልጅ ደግሞ አሰቃቂውን ሞት የሚሞተው መቼ ነው? በኢየሱስ ክርስቶስ ባለማመናችን (ዮሐ 8:24) ስጋውን ካልበላን ደሙን ካልጠጣን (ዮሐ 6:53) ወይም እርሱን በልባችን ካላነገስን ነው። ስለዚህ የምንሞተው ሞት ደግሞ የሞት ሞት ነው ዳግም ሕይወት የማይገኝበት ዘላለማዊ ሞት ታርዶ እንደመሞት አሰቃቂ የሆነ ሞት። ስለዚህ በእኔ ያላመኑትን የሞት ሞትን እንዲሞቱ ፍረዱባቸው ለማለት እንደሆነ እንረዳለን ማለት ነው። ይህም ተነግሯቸው ወንጌል ተሰብኮላቸው አላምንም በማለታቸው ይባስም ብለው ለወንጌሉ ጠላት የሆኑትን ነው ማለት ነው።
May 09, 2022