ጥያቄ ለክርስትያኖች:- 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1:3 የርኅራኄ አባት የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ። እዚህ ጥቅስ ላይ አምላክ እንዳለው ወይም ሌላ አምላክ እንዳለ እያሳየን ነው ስለዚህ ሁለት አምላክ ነው ያለው ወይንስ እየሱስ ጌታ ሲባል አለቃ ወይም መምህር ለማለት የአክብሮት ነው?
May 08, 2022በረከቱ በኛ ላይ ትደርና ሊቁ ቅዱስ ዩሐንስ አፈወርቅ በትርጓሜው እንዲኅ ይለናል። #እነሆ ርሱ ጳውሎስ አብን አምላኩ ለክርስቶስ አለው በውኑ ወልድ ክርስቶስ በክብር ከአባቱ ያንሳልን ? ከአብስ አያንስም ደፍሮ ይኽነን የሚናገር ማንም ሰነፍ የለም መጽሐፍ ለአባቱ አንድ ልጅ እንደመኾኑ እንደ አባቱ ክብር ያለ ክብሩን አየን ያለ አይደለምን (ዩሐ 1.14/ 14:8-11 / 1ቆሮ 12 .3 ) ነገር ግን እርሱ በዚኽ ክርስቶስ በእውነት ሰው እንደኾነ አስረዳን ዳግመኛም በተነሣ ግዜ ከዚኽ አዳም ባሕርይ ሰው መኾኑን አስረዳ ፈጽሞ ከርሱ ወደአልተለየው ወደ አብም ከማረጉ አስቀድሞ ለደቀመዛሙርቱ አምላኬ አምላካችኁ አለ ይኽንን በሰሙ ግዜ ይኽን የተናገረ ሥጋ ብቻ እንዳይመስላቸው ሰው የኾነ ርሱ እግዚአብሔር ቃል አስቀድሞ አቡየ ብሎ ከዚኽ በኄላ አምላኪየ አለ እንጂ (ዮሐ 20:17) እኔ ሰው የኾንኁ አምላክ ነኝና እኔም አንድ ነኝና ይኽነንም ያነንም እኔ እላለኁ ይላል። የሰውን ባሕርይ ገንዘብ አድርጌያለኹና ኀጢአት የሌለበት ርሱ እኔ ነፍስን ሥጋን በእውነት ተዋሐጄ አለኹና ከእኔ ጋር አንድ አካል አንድ ባሕርይ ላደረግኹት ለሥጋ ሥርዐት እንደሚገባ እንዲኽ አባቴን አምላኪየ ብዬ ጠራኹት ይላል ስለዚኽ አንድ ሥርዐትም ሐዋርያ አምላኩ አለ በዚኹ ሥርዐትም ጌታ ይለው ዠመረ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አለ ሰው የኾነ አምላክ እንደኾነ መናገሩ ነው የክብር ባለቤት አለ እግዚአብሔር የሰጠንን ጸጋ ክብር ስብሐት አለው እንዲኹ የምሕረት መገኛ የፍጹም ክብር ባለቤት ባለጊዜም እግዚአብሔር ለኛ ያደረገልንን የቸርነቱን ብዛት በዚኽ ክፍል እንዲኽ አስረዳን።
May 09, 2022