ሰላም ቤተሰቦቼ ሰው ሁሉ በጣም የፈዘዘ ነው ብለው ያወሩብኛል ኧረ እንዳንዶቹማ መጥተው ሁላ አትፍዘዝ ነቃ በል ምናምን ይሉኛል ምን እንደነካኝ አላውቅም ። ከድሮ ጀምሮ በጣም ዝምተኛ ነኝ እና ምንም አላወራም አሁን ላይ በጣም ችግር እየፈጠረብኝ ነው። በስራዬ እራሱ በጣም ተፈላጊነት እያጣሁ ነው የእኔን project እሱ በስነስርዓቱ አይሰራውም ፈዛዛ ነው ተብዬ ለሌላ ሰው ተሰጠ ምን ላድርግ ምንም አይነት ሱስ የለብኝም ፍቅርም አልያዘኝም እስቲ የምታውቁትን ከዚህ ሁኔታ የሚያወጡ መጽሀፍ ወይም ማንኛውንም ነገር ካላችሁ ንገሩኝ
May 05, 2022*በራስህ ኮንፊደንስ ይኑርህ። * የፈለከውን ተናገር/አውራ (ሰው ምን ይለኛል በሚል ሀሳብ በፍፁም ከጭንቅላትህ አውጣው) * ያንተን ውሳኔ ማንም እንዲቀይር አትፍቀድ። * ከዚህ ባህሪህ ጋር የተገናኘ ያለፈ ታሪክ ካለህ ለመርሳት ሞክር። *ከጓደኞችህ፣ ቤተሰቦችህ እና የቅርብ ሰወች ጋር አድማጭ ብቻ ሳይሆን መናገር/መከራከር/መቀለድን በደንብ ተለማመድ። *የሳይኮሎጂ መፅሀፍትን አንብብ። * ለስላሳ ሙዚቃወችን፣ የፍቅር ( Romantic ) ፊልም የምታይ ከሆነ ቀንስ/አቁም። በተቃራኒው በሙዚቃ፡ Rap, Electro Beat... ሙዚቃዎችን አና ፊልም፡ Action, comedy...አይነት ፊልሞችን ብታይ መልካም ነው። ይመችህ✌️
May 05, 2022