can you please tell me the requirements for extension undergraduate program by diploma at commerce?
May 04, 2022Application for Extension Undergraduate Addis Ababa University would like to invite Applicants who want to pursue their studies for Evening Program in the academic year of 2021/22 in Undergraduate Evening program. Online application is mandatory using portal.aau.edu.et. With Regards, Tilahun Tesfaye (PhD) AAU Registrar Requirements: 1. አመልካቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል 2. በዲግሪያችሁ ለምታመለክቱ የወጪ መጋራት ያጠናቀቃችሁበትን የሚገልፅ ደብዳቤ ከትምህርት ማስረጃ ጋር ማቅረብ 3. በዲፕሎማችሁ ወይም ደረጃ 4 ለምታመለክቱ ከትምህርት ማስረጃ ጋር የCOC ደረጃ 4 ማቅረብ 4. ዲፕሎማችሁ የአስተማሪነት ሆኖ ለምታመለክቱ ዲፕሎማ በጨረሳችሁበት የትምህርት አይነት ብቻ በመመዝገብ የትምህርት ማስረጃ ማቅረብ 5. ለPreparatory አመልካቾች ከ2009-2013 ዓ.ም. ድረስ ብቻ ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መስፈርት መሰረት ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብን የምታሟሉ ከትምህርት ማስረጃ ጋር በማያያዝ ማቅረብ 6. ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች በተለያየ የምክንያት አቋርጣችሁ ለምታመለክቱ ከ2009-2012 ዓ.ም. ድረስ ብቻወደ ዩኒቨርሲቲ የገባችሁ በቀን/መደበኛ/ መርሃ ግብር የወጪ መጋራት ያጠናቀቃችሁበትን የሚገልፅ ደብዳቤ ከትምህርት ማስረጃ ጋር በማያያዝ ማቅረብ 7. ማሳሰቢያ 8. ከማመልከቻ ፎርም የሚያገኙትን የማመልከቻ ቁጥር (Application Number) በመያዝ ብር 150 /አንድ መቶ ሃምሳ/ በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ በሞባይል CBE ብር ወይም በወኪሎች ወይም በቅርንጫፍ አማካኝነት በ242424 አጭር ኮድ ክፍያ መፈጸም 9. ክፍያዎትን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ማመልከቻ ፎርሙ በመመለስ በፒዲኤፍ (PDF) ፎርማት የተለወጠ የትምህርት ማስረጃዎትን የወጪ መጋራት ያጠናቀቁበትን ሰነድ መላክ፤ 10. ምዝገባዉ ካከናወኑ በኋላ የትምህርት ማስረጃ በአካል ይዞ በመቅረብ ቢሮ ቁጥር 203 ማስገባት ይኖርብዎታል 11. በዲፕሎማ አመልካቾች የዩኒቨርስቲዉን የመግቢያ ፈተና ጊዜን፤ በዩኒቨርስቲዉ ድረ ገጽ (www.aau.edu.et) እና (https:\\portal.aau.edu.et) ወደፊት ይገለጻል፡፡ 12. ለአዲስ አበባ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለማታ የመጀመሪያ ዲግሪ አመልካቾች በሙሉ በየትምህርት ክፍሉ ፈተና የሚሰጥ መሆኑን ከወዲሁ አውቃችሁ እንድትዘጋጁ እናስታውቃለን፡፡ 13. ለአዲስ አበባ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለማታ ዲፕሎማ የመጀመሪያ ዲግሪ አመልካቾች በሙሉ ከዩኒቨርስቲው መግቢያ ፈተና በተጨማሪም በየትምህርት ክፍሉ ፈተና የሚሰጥ መሆኑን ከወዲሁ አውቃችሁ እንድትዘጋጁ እናስታውቃለን፡፡ 14. የተማሪዎች ቁጥር ከመቀበል አቅም በታች (ዝቅተኛ) ከሆነ የትምህርት ፕሮግራሞች የማይከፈቱ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ 15. በዲግሪያችሁ ለምታመለክቱ የመረጣችሁትን ትምህርት ክፍል የምታገኙት 12ኛ ክፍል ጨርሰው እና በዲፕሎማ አመልካቾች ከተመደቡ በኋላ በሚተርፉ ቦታዎች ላይ ብቻ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ 16. የምዝገባ ቀን፡ ከሚያዚያ24 እስከ ግንቦት 05 2014 ዓ.ም 17. በ2009 ዓ.ም. የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና ወስደው 295 እና ከዚያ በላይ ያላችሁ፡፡ 18. ለPreparatory አመልካቾች ከዚህ በታች የተገለጸለውን የመግቢያ ነጥብ የሚያሟሉ 19. በ2010 ዓ.ም. የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና ወስደው 295 እና ከዚያ በላይ ያላችሁ፡፡ 20. በ2011 ዓ.ም. የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና ወስደው 295 እና ከዚያ በላይ ያላችሁ፡፡ 21. በ2012 ዓ.ም. የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና ወስደው 325 እና ከዚያ በላይ ያላችሁ፡፡ 22. በ2013 ዓ.ም. የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና ወስደው በአንደኛ ዙር በማህበራዊ ሳይንስ 250 እና ከዚያ በላይ ያላችሁ፡፡ 23. በ2013 ዓ.ም. የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና ወስደው በአንደኛ ዙር በተፈጥሮ ሳይንስ 300 እና ከዚያ በላይ ያላችሁ፡፡ 24. በ2013 ዓ.ም. የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና ወስደው በሁለተኛ ዙር በተፈጥሮ ሳይንስ 350 እና ከዚያ በላይ ያላችሁ፡፡ 25. በ2013 ዓ.ም. የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና ወስደው በሁለተኛ ዙር በማህበራዊ ሳይንስ 300 እና ከዚያ በላይ ያላችሁ፡፡ 26. በሚያስገቡት የትምህርት ማስረጃ ላይ የማመልከቻ ቁጥር (Application Number)፣ 27. ያመለከቱትን ሶስት የትምህርት ምርጫዎች እና ስልክ ቁጥር መፃፍ ይኖርብዎታል፡፡ 28. በተጨማሪም ክፍያ ሳይፈፅሙ ዶክመንት ማስገባት ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ Application Date: From May 02, 2022 To May 13, 2022 Application Place: Main Registrar, Admission Office, 2nd Floor, Room No. 203
May 05, 2022