Hey guys edet nachi sle semera uv ena sle welkite mereja kalachihu pleass tebaberugn eski
May 01, 2022ሰመራ UNIVERSITY አድራሻ ❓ 📚 ሰመራ በአፋር ክልል የምትገኝ ዮኒቨርስቲ ነች ። የአየር ሁኔታው ❓ 📚 በጣም ሞቃታማ ነው ስለዚህ ከበድ ያለ ብርድ ልብስ ፈፅሞ አያስፈልግም ይህም ማለት ግን ምንም አይነት አንሶላ አያስፈልግም ማለት አይደለም መጀመሪያ ሴሚስተር ላይ ቀለል ያሉ አንሶላዎች ያስፈልጋችኋል ። የካንፓሶች ብዛት ❓ 📚 ግቢው አንድ ብቻ ነው ምንም branch የለውም። ✅ በግቢው የሚሰጡ ኮሌጆች እንደሚከተለው ተገልጿል ፦ 1.College of engineering and technology 1.1 Chemical Engineering 1.2 Electrical Engineering 1.3 Civil Engineering 1.4 Mechanical Engineering 1.5 Construction Technology & Management (CoTM) 1.6 Water resource & irrigation engineering 2. College of business and economics 2.1 Accounting 2.2 Management 3.college of health science 3.1 Bsc.nursing 3.2 midwifery 4.College of Agriculture 4.1 Narm 4.2 RDA 4.3 Horticulture . . . . . 5.College of Computational science 5.1 Biology 5.2 Chemistry 5.3 Statistics 5.4 6.Language and literature እና ሌሎችም 📚 ማህበረሰቡ በጣም ጨዋ እና ሠው ወዳድ እንግዳ ተቀባይ ነው ። የካፌ ምግብ ❓ 📚 እንደ ማንኛውም ዮኒቨርስቲ ያን ያክል አስደሳች የሚባል አይደለም ፤ የሚቀርቡ ምግቦች ምሳ ላይ ሻል ይላሉ በተረፈ ትንሽ ከበድ ይላል ። ከካፌ ምግብ ውጪ ያሉት❓ 📚 መጀመሪያ ላይ እንደገባችሁም ቢሆን Non-cafe መመዝገብ ትችላላቹ አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ጋ አይቻልም ::ግቢ ውስጥ ቡና 3 ብር (ውጪ ላይ 5 ብር ) ሻይ 2 ብር ምግቦች እስከ 15 ብር (ውጪ ላይ እስከ 25 ብር ) ይገኛሉ ። የረብሽ ሁኔታ ❓ 📚በተረፈ ግቢያችን ከሀገሪቱ ዩንቨርሲቲዎች አንፃር ሲታይ ሰላማዊ ግቢ ነው። የፍቅር ሀገር ነው ። ውሃ ፥ መብራት፤ WIFI ❓ 📚 መብራት አሳሳቢ አይደለም ከነ አይጠፋም ፤ ውሃ እና WIFi በቂ ባይኖንም ለማቅረብ ይሞከራል ። ሽንት ቤት ❓ 📚 የትም ግቢ ካለው አይለይም የፀዳ ባይባልም ፤ ለመጠቀም ያክል ይሆናል ።
May 02, 2022