ሰላም ሰዎች #This_Is_For_Muslims የእስልምና እምነት መተዳደሪያ ህግ (ሸሪያ or Other) ውስጥ የተፃፈ " ዘካ እና ሰደቃ መደረግ ያለበት ለእስልምና እምነት ተከታይ ብቻ ነው" የሚል አለ???
May 01, 2022የዘካተል ፊጥር ዋና ዓላማው ድሆችን በዒድ ቀን ማስደሰት እስከሆነ ድረስ ለዕለቱ እንዲደርስላቸው ገንዘብ ይሁን እህል ለነርሱ የሚሻለዉን መስጠቱ መልካም ነው፡፡ ዘካተል ፈጥር የሚሰጣቸው ወገኖች፡- ዘካተል ፊጥር የሚሰጣቸው ሰዎች ዘካ እንዲሰጣቸው የተደነገገላቸው የኀብረተሰብ ክፍሎች ናቸው፡፡ ግና ለድሆች ቅድሚያ ሊሰጥ እንደሚገባ ዑለሞች ያፀድቃሉ፡፡ የዘካ ድርሻ ለሌላቸው ሰዎች ዘካተል ፊጥርን መስጠት አይፈቀድም፡፡ ዘካተል ፊጥርን ሲሰጡ ለአካባቢ ድሆች ቅድሚያ መስጠት ይገባል፡፡ 1 እና 2. ድሆች (ፉቀራእ)ና ሚስኪኖች የዘካ ዓይነተኛ ዓላማ ድህነትን ማስወገድ ነው፡፡ ኢብን ጀሪር እንዳሉት፡- ‹‹ድሃ (ፈቂር) ሰዎችን የማይጠይቅ ቁጥብ (ሙተዐፊፍ) ችግረኛ ሲሆን÷ ሚስኪን ደግሞ ሰዎችን የሚለምን ችግረኛ ነው፡፡ ለሀብታሞች ወይም ሠርተው የራሳቸውንና የቤተሰባቸውን መሠረታዊ ፍላጎት የማሟላት አቅሙ ላላቸው ሰዎች ከድሆች ድርሻ መስጠት አይፈቀድም፡፡ 3. የዘካ አስተባባሪ ቡድን ከድሆችና ሚስኪኖች ቀጥሎ ዘካ የሚሰጣቸው ወገኖች የዘካን ገንዘብ በመሰብሰብ፣ በማስላትና በመሳሰሉት ተግባራት የተሰማሩ ወገኖች (የዘካ አስተባባሪ ቡድን ሠራተኞች) ናቸው፡፡ 4. ‹‹ሙአልለፈህ ቁሉቡሁም›› (ኢስላምን እንዲላመዱ የሚከጀሉ ወገኖች) አዲስ ወደ ኢስላም የገቡ ሰዎች ከዘካ ድርሻ አላቸው፡፡ ኢስላም ላይ እንዲፀኑና እንዲላመዱ፡፡ 5. ሰዎችን ከባርነት ነፃ ለማውጣት የዘካ ገንዘብ ሰዎችን ከባርነት ነፃ ለማውጣት ሲባልም ወጭ ይደረጋል፡፡ ኢስላም ባርነትን ከምድር ላይ ለማስወገድ ከተጠቀማቸው በርካታ ስልቶች ይህ አንዱ ነው፡፡ 6. ዕዳ ያለባቸው ሰዎች በዕዳ የተያዙና ለመክፈል የተቸገሩ ሰዎችም የዘካ ገንዘብ ባለመብቶች ናቸው፡፡ ዕዳቸውን መሸፈን የሚያስችላቸውን ያህል የዘካ ገንዘብ ሊቀበሉ ይችላሉ፡፡ 7. በአላህ መንገድ (ፊ ሰቢሊልላህ) ‹‹ፊ ሰቢሊልላህ›› ወደ አላህ ሊያደርስ፤ የአላህን እርካታ ለመጎናፀፍ የሚያስችል ማንኛውም መልካም ተግባር ሊሆን ይችላል፡፡ ለምሳሌ የኢስላምን መልዕክት ለሰዎች ማድረስ የሚያስችሉ የዳዕዋ ተቋማትንና ድርጅቶችን ማቋቋም፣ ሙስሊሞችን በትክክለኛ ኢስላማዊና ስብዕና መቅረጽ የሚያስችሉ፣ የተለያዩ ተያያዥ ተቋማትን መገንባትና መዶገም የመሣሠለው ሊሆን ችላል፡፡ 8. በጉዞ ላይ እክል የገጠመው መንገደኛ (ኢብኑ ሰቢል) ወደ ሀገሩ ለመግባት እክል ያጋጠመው መንገደኛ ገንዘብ የሚያገኝበት ሁኔታ የማይመቻችለት ከሆነ ሀገሩ ላይ ባለንብረት ቢሆንም እንኳ ዘካ ይሰጠዋል፡፡ ©️NejashiPP
May 01, 2022