በመ/ቅዱስ ኖህ ከፈጣሪው በተቀበለው ትዕዛዝ መርከቧን አዘጋጀ እና ከእንስሳቱ ከአራዊቱ ከነፍሳቱ ከሁሉም ከሁሉም 2 ሁለት ተባዕት እና እንስት እያደረገ ከቤተሰቡ ጋር ሆኖ ከጥፋት ውሀ እንደዳኑ ተገልፃል። ከጥፋቱ ውሀ በኃሏ አለም ላይ ምንም የቀረ ህይወት ያለው ነገር እንደሌለ መርከብ ውስጥ ያሉት ብቻም እንደቀሩም መ/ቅዱስ ይጠቅሳል። ጥያቄዬ ከጥፉት ውሀ በኃሏ እንስሳቱ አራዊቱ ምናምን እሽ ይሁን የሰው ልጅ እንዴት ሊበዛ ቻለ? ይዞ የገባው ቤተሰቦቹን ከሆነ በነሱ መሀል ግንኙነት ልፈጠር አይችልንም። ምንድን ነው እዚ ጋር ያልተረዳውት ነገር? 🙏 በቅንነት መልሱልኝ
Apr 30, 2022(ኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 7) ---------- 7፤ ኖኅም ስለ ጥፋት ውኃ ልጆቹንና ሚስቱን የልጆቹንም ሚስቶች ይዞ ወደ መርከብ ገባ። . . . 13፤ በዚያውም ቀን ኖኅ ወደ መርከብ ገባ፥ የኖኅ ልጆችም ሴም ካም ያፌትና የኖኅ ሚስት ሦስቱም የልጆቹ ሚስቶች ከርሱ ጋር ገቡ። 👀👀
May 01, 2022