ሂትለር በሚሊዮን የሚቆጠሩ አይሁዶችን ገደላቸው አይደል ያው ባላውቅም አብዛኞቹ ወደ ሲዖል ይመስለኛል እና በሱ ምክንያት ሚሊዮኖች ሲዖል ገቡ። እሱ ግን እንደ ዕድል ሆኖ ንሰሀ ገብቶ ገነትን ቢወርስ በሱ ም/ት ገሀነም የገቡት ሰዎች ዘላለማቸውን ሊቃጠሉ ነውን? ፍትሀዊ ነው?
Apr 30, 2022በሱ ም/ት አንድም ሰው ሲዖል የገባ የለም ሁሉም በየራሱ ሀጥያት ነው የሚጠየቀው። እሱ ንስሀ ቢገባ አዎ ልክ ነህ ገነት ይገባል(ግን ፍርዱ የእግዚአብሔር ነው)።ይሁዳ እንካ አምላካችንን በ30ዲናር በሸጠ ጊዜ ተፀፅቶ ነበር እኮ እንደውም ገንዘቡንም መልሶ ነበር ነገር ግን እግዚአብሔር ይቅር እንደማይለው ማሰቡ ነበር የሱ ትልቁ ሀጥያት ይቅርታ ማለት ሲገባው ታንቆ ሞተ።እንደ ጴጥሮስ ግን ይቅርታ ቢጠይቅ (ንስሀ) ቢገባ ወደ ሲዖል ባልገባ ነበር። ፍትሀዊ ነው ወይ ላልከው.....
May 01, 2022