Hey guys ye Addis ababa university megebya ken meche nw bizu yetlyaye rumour selasemaw please sure yehonachu negrugn 🙏
Apr 29, 202224-28 balew.
Apr 29, 2022Hey guys ye Addis ababa university megebya ken meche nw bizu yetlyaye rumour selasemaw please sure yehonachu negrugn 🙏
Apr 29, 202224-28 balew.
Apr 29, 2022በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2014 የትምህርት ዘመን በመደበኛ የዲግሪ ትምህርት መርሃ-ግብር በትምህርት ሚ/ር መስፈርት መሠረት አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ ከ ሚያዚያ 24 ቀን እስከ ሚያዚያ 28 ቀን 2014 ዓ.ም በተመደባችሁበት የዩኒቨርስቲው ካምፓስ ሪፖርት እንድታደርጉ ያሳውቃል፡፡
Apr 29, 2022በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2014 የትምህርት ዘመን በመደበኛ የዲግሪ ትምህርት መርሃ-ግብር በትምህርት ሚ/ር መስፈርት መሠረት አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ ሚያዚያ 24 ቀን እና ሚያዚያ 25 ቀን 2014 ዓ.ም በተመደባችሁበት የዩኒቨርስቲው ካምፓስ ሪፖርት እንድታደርጉ ያሳውቃል፡፡ ተማሪዎችም ለምዝገባ ስትመጡ፣ ብርድልብስና አንሶላ፣ የአስራ ሁለተኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ዋናውንና ፎቶ ኮፒ፣ ስምንት ጉርድ ፎቶግራፍ ይዛችሁ መምጣት እንዳለባችሁ ያስታውቃል፡፡ የስፖርት ትጥቅ በተጠቀሱት ቀናት ከአዲስ አበባ ውጪ ለሚመጡት ተማሪዎች በመርካቶ አውቶብስ ተራ፣ በላም በረት፣ በአቃቂ እና በአስኮ የመኪና መናኸሪያዎች በመገኘት ዩኒቨርስቲው የትራንስፖርት አገልግሎት ያቀርባል፡፡ ፡ ከተገለጸው ቀን በፊት ለሚመጡ ተማሪዎች ምንም ዓይነት አገልግሎት ዩኒቨርስቲው አይሰጥም፡፡ ለተጨማሪ መረጃ የዩኒቨርስቲን ድረገጽ https://portal.aau.edu.et/ ወይም www.aau.edu.et ማየት የሚቻል ሲሆን ነዋሪነታችሁ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሆኖ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት የምታደርጉትና ስለ ዩኒቨርስቲው ገለጻ የምታገኙት ሚያዚያ 26 ቀን 2014 ዓ.ም መሆኑን ያሳውቃል፡፡ ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትመጡ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው ውስጥ የመኝታ አገልግሎት ለማግኘት የተመደበላችሁን የመኝታ ክፍል 12ኛ ክፍል በተፈተናችሁበት ቁጥር በመጠቀም ከ https://portal.aau.edu.et ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ያሳውቃል፡፡ በተለያየ ምክንያት ትምህርት አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ ውጤታችሁ የሚያበቃችሁ ተማሪዎች አዲስ ከተመደቡ 1ኛ ዓመት ተማሪዎች ጋር በመቅረብ በ2014 ዓ.ም. የመጀመሪያ ሴሚስተር ለመልሶ ቅበላ ከሚያዚያ 27 እና 28 2014 ዓ.ም እንድታመለክቱ እናሳውቃለን፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ Join 👇and Share @AAU_PLATFORM
Apr 29, 2022