There is boy i really want to merry i love him to death yemr gn he said you are smart and konjo so there are other boys who will kill to be with you i am not the person you think i am.......thats what he say but the real thing that happen i guess i used to date his best friend he he said he cant pass this line but he said he cant resist me what do you think i should do yemr teyw......endatlugn bc i tried that one and it only make me love him more ebakachu help me out Thank you for your considering advice in advance
Apr 28, 2022ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ/የባልንጀራህን ንብረት አትመኝ የሚለው የእግዚአብሔርን ሕግ ማሰቡ መልካም ነው። ሕግ ፍቅረ እግዚአብሔርና በፍቅረ ቢጽ ይፈጸማል በመሆኑም አስቀድሞ ባልንጀራው ወዳጁ ከሆነ ሰው ጋር የፍቅር ግንኙነት የነበረሽ ከሆነ በቀጣይ አሁን አፈቅረዋለው ከምትይው ሰው ጋር ለመሆን እጅግ ከባድ ነው በተለይ #ላፈቀርሽው ሰው። አንቺን ባየ ቁጥር የሚያስታውሰው ወዳጁን ነው ። ራስ ወዳድ አትሁኚ። ልጁ ትክክለኛ ውሳኔን ወስኗል ይህ ውሳኔው ለሱ ሕሊና እረፍት ላንቺም ወደፊት ከሱ ጋር ይኖረኛል ብለሽ ለምታልሚው ህልም ሰላም ሰጪ ነው። አንዳንድ ትክክለኛ ውሳኔዎች ከባድ እና ሕይወትን ባልተመለከትንበት አቅጣጫ የሚዘውሩ ናቸውና የልጁን እምቢታ እንደ በጎ ገፀበረከት አሜን ብሎ መቀበል የግድ ያስፈልጋል። #ተይው። መተው ማለት መርሳት ማለት ግን አይደለም። መተው ማለት በጎን ነገር ተምሮ ማለፍና ልብን የተሻለ አፍቃሪ ማድረግ ማለት ነው። የተሻለ አፍቃሪ ማለት አሁን ለልጁ አለኝ ከምትይው ፍቅር በላይ አስቀድሞ ራስሽን መውደድ በዚህም ደሞ የተሻለና ደስተኛ ሕይወት እንደሚገባሽ በማመን ለራስ ካለሽ ፍቅር በላይ ሌላን ሰው መውደድ ማለት ነው። #ተይው እህቴ
Apr 29, 2022