hey guys i just wanna know if there is anyone here who is or has been to Gambela university. my friend was placed there and she is freakin out so we're in need of any information we can get please help
Apr 26, 2022I think this helps Gambela University ‼️ ሰላም ውድ ቤተሰቦቻችን እንዲሁም አንባቢዎች ዛሬ ቤታችን ይዞላችሁ የቀረበው ስለ ዩኒቨርስቲይ መረጃ ከአባላቶቹ በደረሰው information መሰረት አሰባስቦ ጨርሶ እንካችሁ ይላል። #GAMBELLA University ግቢያችን ይለናል አንድ የ3ተኛ ዓመት የ civil engineer ተማሪ "በጣም ልዩ ነው በአረንጓዴ እጽዋት እና በለምለም አፈር ውስጥ የተሰራ ትልቅ ተቋም ነው። የትምህርት ጉዳይ ግቢያችን አይወቀስም። የ4ተኛ ትውልድ ከመሆኑ ጋር ስናስበው ግንባር ቀደም ያስብለዋል። የ medicine ግቢ ሊሆን ከወዲሁ እንቅስቃሴውን አቀላጥፎ ሜዲካል ካምፓሱን በማቀላጠፍ ላይ ነው። በቅርቡ አጠናቆ ውድና ብርቅዬ የጤና መኮንኖችን ብቁ ያረጋል ባይ ነኝ። ምግብ ብዙም የሚጋነን ባይሆንም ምቾት አይነፍግም። ደስ የሚለው ከደበረህ/ሽ ወጣብለህ/ሽ በፍራፍሬ ሆድሽን ጥዝር አርገሽ/ህ መግባት መቻልሽ ነው። ቤተሰባችን ሙዝ ቢያምሮት እኛ ሀገር ላይ የበረሀዋ ገነት ጋምቤላ ክልል ገብተው አትክልት የ 10 ብር በሸክም ነው። ቡና 5 ብር ከፍለው ሶስት ቀን ጥም ቆራጭ ነው። ሻይ 5 ብር ከከፈሉ ምርቃት ዳቦ አለው ብል ማጋነን አይሆንብኝም ለምን ብትሉ አሪፍ መስተንግዶ ያገኛሉ። ወዳጄ ወንድ ነህ ስልክ ካለህ ከኪስህ እንዳይወጣ ኪስህን በጂህ ካሊያዝክ ኪስህ ያሾልካል። ባጭሩ የሱዳን ቅባት ያላቸው ነፍ የከተማችን ጭልፊቶች አሉ። ሴት ነሽ እንዴ እህታችን ከ መሼ ወደ ከተማ ውስጥ ከገባሽ አንዳንድ ዱርዬወች አሉ እመኒኝ ከወር በኋላ ቦርጭ ይጠብቅሻል። ከከተማው ወጣ ያለ በመሆኑ ግቢው በሰላሙ ግባር ቀደም ነው። ዘረኝነት አደለም ሊኖር ሊታሰብ አይችልም ጠፈር ላይ ያላችሁ እስኪመስላችሁ ሁሉም ልዩነቱን እረስቶ ህልሙን ሊያሳካ ይሮጦል። ውሃ ጠፋ ማለት ልማዱ ነው እሚያስብ አይደለም ግን ከሳምንት አንድ ቀን አይቀሬ ነው። የግቢው ህግ ጠበቅ ይላል ምክንያቱም ግቢው አላማውን ያቀዋል ብቁ ተማሪ ለማውጣት ቁንጥጫ አይዘነጋም ቁጥጥር ሀርድ ነው። አዬር ሁኔታ ሶስት አይነት ሲሆን ክረምት በጋ ብቻ ሳይሆን ሞቃትም አይነት አለው ከታህሳስ ወር-ማዚያ መገባደጃ ሙቀቱ ለመማር አደለም ለመዝናናት ይረብሻል ግቢው ያንን ያገናዘበ ቤንት ኔተር ስላለው አያሳስብም። የሙቀት መጠኑ ከ36°c-45°c ይደርሳል። ከመስከረም -ህዳር እኩሌታ ምርጥ የአዬር ሁኔታ ሲኖረው መለስተኛ የዝናብ መጠን ይስተዋላል። ብርድ ግን ይናፍቃችኋል። ከሰኔ-ነሀሴ ወር የዝናብ ጋጋታ ተውኝ ግን ያን ያክል አያስመርርም ምቾት ይሰጣል። ትንሽ ቅዝቃዜ አይጠፋም ሹራብ ለብሰው ግን ሙቀት መረበሹ አይቀርም። መዝናኛስ ካሉኝ መዋኜት ሁሉ ብቃት ካላችሁ ባሮ ገብታችሁ ደቡብ ሱዳን ጁባ መውጣት ይቻላል ግን ቬዛ አይሰጡም😂 ማብራት አይጠፋም ኔቶርካችን ባለበት ኮንድሽን ላይ ነው።ቢዚ ቢዚ አንዳንዴ መገኛ በበረሃዋ ገነት በጋምቤላ ክልል ውስጥ ሲሆን ዋና ከተማው ውስጥ መሆኑ ብቸኛ ያረገዋል። የግቢ ብዛቶች ለጊዜው አንድ ለእናቱ በቅርቡ medicine ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል። ዋናው ግቢ ከመሀል ከተማ የ 30 ደቂቃ ጉዞ ይርቃል ያ ማለት 2.1 km ሲሆን እንደልብ የታክሲና ባጃጅ ተሽከርካሪ ስላለ አያሳስብም። ጥንቃቄ ግድ ይላል። ይሰመርበት አሞራ ነፍ ነው። ግቢው አሁን ላይ ብዙ የትምህርት ዘርፎች ይሰጣል። #በnatural ዘርፍ -Civil engineer -Computer since -Irrigation and Water Resource Engineering -Food Process Engineering -Mechanical engineer -Chemical Science Labortory Technology ..... Chemistry Biology Mathematics Physics Statics #የSocial ዘርፍ -Logistics and Supplies Management -Logistics and Supply chain Management -Management -Marketing Management -Public Administration and Development management -Educational Planning and Management -Economics -Disaster Risk Management and Sustainable Development #የጤናው ግቢ ሁለተኛው ግቢ ሲሆን 5km አከባቢ ይርቃል ከዋናው ግቢ። በቅርቡ አጠናቆ ውድና ብርቅዬ የጤና መኮንኖችን ብቁ ያረጋል። #Wifi አባቱ ቅንጦት ነው ሲያምርህ ይቀራል አንዳንዴ 2G+ ብልጭ ይላል 2 mb 2:00 ይፈጃል። 3G+ እንደሚያሳይ ዛሬ የደረሰኝ መረጃ ነው። ማብራት ፏ ነው ይመስጣል አጠፋፉ ቀልብህም ተከትሎት እልም ይላል። አውቶማቲክ ጄነነተር አስገብቷል። ወዳው ነፍስህ ትገባለች #ውሃ ግቢ ቢጠፋ መንገድህ ጠቅላላ ውሃ አይደል አሳ እንዳያንቅህ በጨርቅህ ጠጣ። ንፅህናው ግን ብዙ አያማርርም መሻሻል ይታያል። የግቢ አጥር ዝግ ነው። #ዶርም ሎከር ከስንት አንድ ችግር ቢኖርበት እንጂ ህንፃዎቹን ያማከለ ውበት አለው ያምራል። #ሽንት ቤት የብዙ ግቢ ችግር ነው ግን እዚህ ግንባር ቀደም ሆኗል። መረጃ ና አስተያየት ለመስጠት 👉 @Ethiostudent4bot ለተጨማሪ የ 12ኛ ክፍል መረጃዎች🙏 🔥@hahuethiopia1 🔥 🔥@hahuethiopia1 🔥 🔥@hahuethiopia1 🔥
Apr 28, 2022