Sewoch please tebaberugh ka ASTU wade AASTU mikyreghe saw aginche naber ena universitiw eshi ylal? 🙏 mokro miyak kalew its urgent pls
Apr 25, 2022ቀን 18/08/2014 ዓ.ም በ፡ሁለቱ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ለተመደባችሁ ተማሪዎች እና ጉዳዩ ለሚመለከታችሁ በተሰቦችና ተማሪዎች በሙሉ ጉዳዩ፡ ምደባን አስመልክቶ እና በተደጋጋሚ ለሚጠየቁ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠትን ይመለከታል፡፡ በሁለቱ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ተመድባችሁ የተለያዩ ጥያቄዎችን በስልክና በተለያዩ መንገዶች ጥያቄ እያቀረባችሁ መሆኑን ተረድተናል፡፡ ለእያንዱ ተማሪ በስልክ ምላሽ መስጠት በጣም አድካሚ በመሆኑ እየተነሱ ላሉ ጥያቄዎች ጠቅለል ያሉ መልሶችን በሚመለከተው መልኩ አቀርበናቸዋል፡፡ ጥያቄ ቁጥር አንድ፡ የኔ ምርጫ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ነበር የተመደብኩት ግን አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ነው መቀየር አይቻልም ወይ ወይም በተቃራኒው ? መልስ፡ ምደባው የተከናወነው ተማሪዎች ባስመዘገቡት ውጤት መሰረት ሲሆን የተሻለ ነጥብ ያስመዘገቡ በመጀመሪያ ምርጫቸው ተመድበዋል፡፡ አሁንም የተሻለ ውጤት ያላቸው በሁለተኛ ምርጫቸው ከመጀመሪያ ምርጫቸው ውጪ ተመድበዋል፡፡ ጥያቄ ቁጥር ሁለት፡ አልፈው ወደ ዩኒቨርሲቲዎቹ መግባት በማይፈልጉ ተማሪዎች ወይም በእርስ በእርስ መቀያየር አይቻልም ወይ? መልስ፡ ቅያሬም ይሁን የእርስ በእርስ ለውጥ ፈፅሞ የማይፈቀድ ሲሆን ሁለቱም ዩኒቨርሲቲዎች ከዚህ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን አያስተናግዱም፡፡ ሁሉም ተማሪ በተመደበበት ዩኒቨርሲቲ ብቻ ነው መማር የሚችለው፡፡ ጥያቄ ቁጥር ሶስት፡ በተለያዩ ምክንያቶች የመግቢያ ፈተናውን መፈተን አልቻልንም፤ ድጋሜ ፈተና ዩኒቨርሲቲዎቹ ይሰጣሉ ወይ፡፡ መልስ፡ ሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች የመግቢያ ፈተናውን ሰጥተው ምደባ ያከናወኑ በመሆኑ ድጋሜ የፈተና ጊዜ በማውጣት ተማሪዎችን አይቀበሉም፡፡ አንድ ተማሪ የፈተና ጊዜ ካለፈበት ሌላ የማካካሻ ፈተና አይዘጋጅለትም፤ ሊዘጋጅለትም አይችልም፡፡ ጥያቄ ቁጥር አራት፡ ከ ሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች ምደባ አውጡንና በትምህርት ሚኒስተር እንድንመደብ አድርጉን፡፡ መልስ፡ በሁሉቱ ዩኒቨርሲቲዎች አንድ ጊዜ ከተመደባችሁ በኃላ ወደ ትምህርት ሚኒስተር መልሶ ምደባ እንዲረግላችሁ ማድረግ በፍፁም አይቻልም፡፡ ተማሪዎቹ በተመደቡበት ዩኒቨርሰቲ ብቻ እንዲማሩ ነው የሚደረገው፡፡ ጥያቄ ቁጥር አምስት፡ በተለያዩ ከህክምና ክትትልና በሽታ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች በልዩ ሁኔታ በሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች መመደብ አንችልም ወይ የሚሉ ጥያቄዎች እየተነሱ ይገኛሉ፡፡ መልስ፡ ከበሽታ እና ህክምና ክትትል ጋር ለተያያዙ ጥያቄዎች እንዲሁም ምደባ ምላሽ የሚሰጠው ትምህርት ሚኒስቴር እንጂ ሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች እንዳልሆኑ አውቃችሁ ጥያቄዎቻችሁን ለሚመለከተው የመንግስት ተቋም ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ ወደ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ጥሪን አስመልክቶ በዩኒቨርሲቲው መገናኛ ዘዴዎች የምንገልፅ በመሆኑ አባል በመሆን ትክክለኛ መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ University Official Website: www.aastu.edu.et University Official telegram channel፡ https://t.me/pir2011 University Official Facebook Account: https://www.facebook.com/aastu.edu.et University Official You tube Channel: https://www.youtube.com/channel/UCUpgXuqDCiLfgLPK_FxS-6g ህዝብና አለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
Apr 26, 2022