ዉዶች እንዴት ናችሁ? ሴት ነኝ። 29 አመቴ ነዉ። ስራ እሰራለሁ መልኬም ደህና ነዉ። ፍቅር የሚባል ነገር በህይወቴ ይዞኝ አያቅም። ድራማ ነዉ የሚመስለኝ። ለማግባት ጭራሽ አስቤ አላዉቅም። እፀልያለዉ፣ፀበልም እጠመቃለሁ! ልቤን ምን እንደደፈነዉ ላዉቅ አልቻልኩም። እንደዚህ አይነት በሽታ አለ ሰዎች? እንደኔ የሆናችሁ ሴቶች አላችሁ? ለ 2ሳምንት የማቀዉ ሰዉ የምጠጣዉ መጠጥ ላይ የእንቅልፍ ኪኒን ጨምሮብኝ ድንግልናዬን ከወሰደ ወደ 7 አመት ይሆነዋል። በሱ ምክንያት ወንዶችን እንዳልጠላ አይምሮዬን አሳምኜ ነበር በወቅቱ። ምን አልባት የሱ ተፅዕኖ ይሆን ያሰረኝ ወይስ ሌላ ምክንያት አላዉቅም። በቃ ህይወት ድብር ይለኛል አንዳንዴ። ለማንም ሀሳቤን ስለማላካፍል አንዳንዴ በጣም ተስፋ እቆርጣለሁ። እራሴን ባጠፋ ብዬም ብዙ ጊዜ አስባለሁ። ብቻ ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላዉቅም አለም ግልብጥብጥ ብሎብኛል ምከሩኝ። ምን ላድርግ? ዓለም ያለ ፍቅር መኖር ያስጠላል ልቤ ደሞ ድንጋይ ሆኖብኛል😢😢😢😢
Apr 25, 2022ይህ ችግር እንዲለቅሽ ወደ ህይወትሽ ሊገባ ያለን ወንድ በሩን አትዝጊበት አልችልም አልፈልግምን ትተሽ ሞክሪ ..በትክክል ይሆነኛል የምትይውን ወንድ ምረጪ ከልብሽ ቅረቢው እሱ ታሪክን ይቀይርልሽ ይሆናል
Apr 25, 2022