#technology
ሰላም ሰላም እንዴት ናችሁ። በዚ ሳምንት ነበር ስልኬን የተሰረቅኩ እና ሲሙን በጊዜው እንዲቆረጥ አልጠየኩም ነበር ። ሌቦችም በሲሙ ወንጀል ሰሩበት ። ከጠፋብኝ ከ2 ቀን በሗላ ሲሙን ወደ ethio tele ሔጄ ላዎጣ ስጠይቅ አዘጋው አሉኝ አዘጋሁት አሁን ደሞ አስከፍተው እና እንስጥህ አሉኝ። # ላስከፍት ስል በሲሙ ወንጀል ተሰርቶበታል አሁን መከፈት አይችልም በመጣራት ላይ ነው አሉኝ ። በአቅራቢያህ ወደሚገኝ ethio tele ሔደህ የሚሞላ ፎርም አለ ሙላ አሉኝ ሁኔታውን አስረድቼ ፎርም ልሙላ ስራቸው የለም ፎርም የሚባል ነገር ተሞልቶ አያውቅም አሉኝ ። ሲሙ በጣም ያስፈልገኛል ብዙ ሰዎች ጋ የምገናኝበት ቋሚ ሲም ነበር የስራ ማስታዎቂያ ሞልቼ የምጠባበቅበት ነበረ ። እባካችሁ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ክራችሁን ለግሱኝ? ሌላ አማራጭ አለኝ?
Apr 25, 20224 engagements