ርዕስ: ነብዩ ሙሐመድ የእዝነቱ ነብይ ደራሲ: ኡስማን ኑሪ ቶፕባሽ ተርጓሚ: ሙኒራ አልመናን በቱርካዊው ደራሲ ተፅፎ በሙኒራ አልመናን ወደ አማርኛ የተተረጎመው ይህ መፅሀፍ የነበዩ መሀመድ ዋነኛ መገለጫ በሆነው እዝነት ላይ የሚያተኩር ነው። @kooblife @kooblife #Join & share
Apr 20, 2022ርዕስ: ነብዩ ሙሐመድ የእዝነቱ ነብይ ደራሲ: ኡስማን ኑሪ ቶፕባሽ ተርጓሚ: ሙኒራ አልመናን በቱርካዊው ደራሲ ተፅፎ በሙኒራ አልመናን ወደ አማርኛ የተተረጎመው ይህ መፅሀፍ የነበዩ መሀመድ ዋነኛ መገለጫ በሆነው እዝነት ላይ የሚያተኩር ነው። @kooblife @kooblife #Join & share
Apr 20, 2022Rየታላቁ አዛኝ የአለም ነብይ ጣፋጭ ታሪክ (ሲራ) ክፍል 1⃣ @Sycotube 🕋 የነብዩ የዘር ሐረጋቸው፣ አወላለዳቸው እና የልጅነት ዘመን 🥀 ሙሐመድ የዐብደላህ ልጅ፣ የአብዱል ሙጦሊብ ልጅ፣ የሃሽም ልጅ፣ የመናፍ ልጅ፣ የፈህር (ቁረይሽ) ልጅ፣ የማሊክ ልጅ፣ የነድር ልጅ፣ የኪናነህ ልጅ፣ የዐድናን ልጅ፣ የአላህ ነብይ እስማዒል ልጅ፣ የአላህ ወዳጅ የኢብራሂም ልጅ። አላህ ከጥሩ ጎሳ መረጣቸው። የመሐይምነት ዘመን ቆሻሻ ወደ ዘር ግንዳቸው አልገባም። 📜 ሙስሊም እንደዘገቡት የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “አላህ ከእስማዒል ልጆች ኪናናን፣ ከኪናናህ ልጆች ውስጥም ቁረይሽን፣ ከቁረይሽ ሃሽምን፣ ከበኒ ሃሽም በኩል ደግሞ እኔን መርጧል።” (📚ሙስሊም ዘግበውታል) 🌐 አወላለዳቸው የተወለዱት የዝሆን አመት (ዓመል ፊል) በመባል በሚታወው ዘመን ነው። ይህም ዓመት አብረሃ ካዕባን ለማፍረስ የሞከረበት ኣመት ነበር። አላህም እጅግ በሚያስደንቅ ጥበብና ተአምር ሐሳቡን አምክኖታል። ይህ በቁርአን ታሪክ ተወስቷል። ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) በዚሁ አመት በወርሃ ረቢአል አወል 11ኛው ቀን በእለተ ሰኞ እንደተወለዱ ዘገባዎች ያመለክታሉ። 🌐 አስገራሚ ጅምርና ግልጽ በረከት አባት አልባ ሆነው ተወለዱ። እናታቸው እርሳቸውን የሁለት ወር እርጉዝ እያለች አባታቸው ሞቱ። አያታቸው ዐብዱል ሙጦሊብም የማሳደግ ሐላፊነቱን ወሰዱ። በያኔዎቹ ዐረቦች ባህል መሠረትም ከበኒ ሰዕድ ጎሳ የሆነችና ሐሊመት ቢንት አቢ ዙዓይብ የምትባል እንስት ታሳድጋቸው ዘንድ ተሰጣት። የታሪክ ጸሐፊዎች እንደሚስማሙት ያኔ የበኒ ሰዕድ ቀዬ በድርቅ የተመታበት አመት ነበር። የእንስሳት ጋቶች ነጥፈዋል። አዝርእቱ ደርቀዋል። ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) በሐሊማ ቤት ካረፉበት እና ጡቷን መጥባት ከጀመሩበት ቅጽበት አንስቶ ግን የሐሊማ ቤት በበረከት ተሞላ። ፍየሎቿ ጠግበውና ጋቶቻቸው በወተት ተሞልቶ ይመለሱ ጀመር። በበኒ ሰዕድ መስክ ላይ እያሉ የተከሰተው የደረታቸው መቀደድ አላህ ለትልቅ ሐላፊነት እንደመረጣቸው የሚጠቁም የነብይነት ምልክት ነበር። አነስ ኢቢን ማሊክን (ረ.ዐ) ዋቢ በማድረግ ሙስሊም እንደዘገቡት የአላህ መልእክተኛ በልጅነታቸው ዘመን ከሕጻናት ጋር በመጫወት ላይ እያሉ ጅብሪል (ዐ.ሰ) መጣና ያዛቸው። አጋደማቸውም። ደረታቸውንም ሰነጠቀው። ልቦናቸውንም አወጣ። የረጋ ደም የሚመስል ነገርም ከውስጡ አስወገደ። “ይህ የሰይጣን ድርሻ ነው” አለም። በወርቅ ሳህን ውስጥ አድርጎም በዘምዘም ውሃ አጠበው። ከዚያም እንደነበር ጠገነውና ወደቦታው መለሰው። ልጆችም ወደ ሐሊማ ቤት እየሮጡ ሄደው “ሙሐመድ ተገደለ” በማለት ተናገሩ። ሲመጡ የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ፊት ገርጥቶ አገኙት። አነስ፡- “የዚህን ክስተት ፋና ከነቢዩ ደረት ላይ አይቻለሁ” ሲሉ ተናግረዋል። ከልባቸው ውስጥ የረጋ ደም የሚመስል ነገር መወገዱ እርሳቸውን ከልጅነት አጓጉል ባህሪያት አርቆ፣ ቁም ነገረኛ፣ ጽኑ፣ ሚዛናዊና ውብ ባህሪያት የተላበሱ ለማድረግ ነው። አላህ በጣም እንደሚጠብቃቸው እና እንደሚንከባከባቸው፣ ሰይጣንም እርሳቸውን የመተናኮል አቅም እንዳይኖረው መደረጉን ለማመልከትም ጭምር ነው። (📚ፊቅሁ ሲራ – ዶክተር ረመዷን አል-ቡጢ) ይህ ክስተት ሐሊማ ሕጻኑን ወደ ቤተሰቦቹ እንድትመልስ ምክንያት ሆነ። ያኔ የነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) እድሜ አምስት አመት ነበር። ስድስት አመት ሲሞላቸው እናታቸው አሚና ሞተች። አያታቸው ሊያሳድጓቸው ወሰዷቸው። ስምንት ዓመት ሲሞላቸው አያታቸው ሞቱ። የማሳደጉን ሐላፊነትም አጎታቸው አቡ ጧሊብ ወሰዱ። 🌐 የላቀ እጣ ፈንታ አስራ ሁለት አመት ሲሞላቸው አጎታቸው አቡ ጧሊብ ወደ ሻም ለንግድ እርሳቸውን አስከትለው ወጡ። ቅፍለቱ በስራህ በተባለ ቦታ ላይ ሲያርፍ ቡሐይራ የተባለን አንድ መነኩሴ ለመጎብኘት ጎራ አለ። ሰውየው የክርስትና ሐይማኖትና መጽሐፍት አዋቂ ነው። ነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) በትኩረት አስተዋላቸው። በጥንቃቄ አጠናቸው። አናገራቸውም። ከዚያም ወደ አቡ ጧሊብ በመዞር፡- “ይህ ልጅ ምንህ ነው?” አላቸው። “ልጄ ነው” አሉት። (አቡ ጧሊብ በጣም ስለሚወዷቸው ልጄ በማለት ነበር የሚጠሯቸው።) ቡሐይራም፡- “ልጅህ አይደለም። የዚህ ልጅ አባት በሕይወት ሊኖር አይችልም” ሲል ተናገረ። አቡ ጧሊብም “የወንድሜ ልጅ ነው” አሉ። “አባቱ ምን ሆነ?” ሲል ጠየቃቸው። “ተረግዞ እያለ ሞተ” አሉ። “እውነት ብለሐል። በአስቸኳይ ወደሀገሩ ይዘኸው ተመለስ። አይሁዶች እንዳያገኙት ተጠንቀቅ። በአላህ እምላለሁ ካገኙት ይተናኮሉታል። ለታላቅ ደረጃ የሚበቃ ልጅ ነው” አላቸው። አቡ ጧሊብም ፈጥነው ወደ መካ መለሱት። 🌐 እንጀራ ፍለጋ የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ለወጣትነት እድሜ ሲደርሱ እንጀራ ፍለጋ መሮጥ ጀመሩ። ፍየል ጥበቃ የጥረታቸው መጀመሪያ ነበር። በኋላ ላይ፡- “ለመካ ሰዎች በቀራሪጥ (መጠነ ትንሽ ክፍያ) ፍየል እጠብቅ ነበር።” ሲሉ ተናግረዋል። ክፍል ሁለት ይቀጥላል....... @Sycotube Ezi channel lay yelkekal join bleh/sh anbeb
Apr 20, 2022በዩቱዩብ እኮ ነፍ ነው የረሱል ታሪክ
Apr 20, 2022