መልሱ የኔ አይደለም አብዛኞቹንም አላቃቸውም ነበር!
Apr 19, 2022መልሱ የኔ አይደለም አብዛኞቹንም አላቃቸውም ነበር!
Apr 19, 202222 sm idk አብ ማለት አባት አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር ከኛ ጋር ይሄንን ነዋ ማውቀው
Apr 19, 2022እግዛብሔር ሳይሆን እግዚአብሔር ነው፡፡እና 1.አሌፍ ፡ አሌፍ ብሂል አብ ፈጣሬ ኩሉ ዓለም ዓለምን ከነጓዟ ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ የፈጠረ እግዚአብሔር ነው ማለት ነው። 2. ቤት፡ ቤት ብሂል ባዕል እግዚአብሔር እግዚአብሔር ሁሉን መስጠት የሚችል ቸር ለጋስ ባለጸጋ ነው ማለት ነው። 3. ጋሜል ፡ ጋሜል ብሂል ግሩም እግዚአብሔር እግዚአብሔር ሊመረመር የማይችል ግሩም ድንቅ ነው ማለት ነው። 4. ዳሌጥ ዳሌጥ ብሂል ድልው እግዚአብሔር እግዚአብሔር ፍጥረታትን ሁሉ ፈጥሮ ያዘጋጀ ነው ማለት ነው። 5. ሄ፡ ሄ ብሂል ህልው እግዚአብሔር እግዚአብሔር በአንድነቱ በሦስትነቱ ለዘለዓለም ይኖራል ማለት ነው። 6. ዋው ፡ ዋው ብሂል ዋህድ እግዚአብሔር እግዚአብሔር በመንግሥት በሥልጣን በአገዛዝ በባህርይ አንድ አምላክ የሆነ ማለት ነው። 7. ዛይ ፡ ዛይ ብሂል ዝኩር እግዚአብሔር እግዚአብሔር በሥራው ሁሉ እየታሰበ ሲመሰገን የሚኖር ፈጣሪ ነው ማለት ነው። 8. ሔት ብሒል ሕያው ሔት እግዚአብሔር በመንግሥቱ ሽረት በባሕርዩ ኅልፈት የሌለበት ለዘለዓለም ሕያው የሆነ ነው ማለት ነው። 9. ጤት ፡ ጤት ብሂል ጠቢብ እግዚአብሔር እግዚአብሔር ጥበብን የሚገልጽ ከጥበበኞች ይልቅ ጥበበኛ የሆነ አምላክ ነው ማለት ነው። 10. ዮድ፡ ዮድ ብሂል የማነ እግዚአብሔር ገብረት ኃይለ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለ እሱ ኃያልና ጽኑዕ የሆነ ነው ማለት ነው። 11. ካፍ ፡ ከሀሊ እግዚአብሔር ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የሌለ ሁሉን ማድረግ የሚቻለው አምላክ ነው ማለት ነው። 12. ላሜድ ፡ ላሜድ ብሂል ልዑል እግዚአብሔር እግዚአብሔር ልዑለ ባሕርይ የሆነ አምላክ ነው ማለት ነው። 13. ሜም ፡ ሜም ብሂል ምዑዝ እግዚአብሔር እግዚአብሔር ንጹሕ ባሕርይ የሆነ አምላክ ነው ማለት ነው። 14. ኖን፡ ኖን ብሂል ንጉሥ እግዚአብሔር እግዚአብሔር የነገሥታት ንጉሥ የገዥዎች ገዥ የሆነ አምላክ ነው ማለት ነው። 15. ሳምኬት ፡ ሳምኬት ብሂል ሰፋኒ እግዚአብሔር እግዚአብሔር ሁሉን የሚገዛ አምላክ ነው ማለት ነው። 16. ዔ፡ ዔ ብሂል ዓቢይ እግዚአብሔር እግዚአብሔር ታላቅና ገናና የሆነ አምላክ ነው ማለት ነው። 17. ፌ፡ ፌ ብሂል ፍቁር እግዚአብሔር እግዚአብሔር ተወዳጅ የሆነ አምላክ ነው ማለት ነው። 18. ጻዴ፡ ጻዴ ብሂል ጻድቅ እግዚአብሔር እግዚአብሔር ሐሰት የሌለበት እውነተኛ አምላክ ነው ማለት ነው። 19. ቆፍ፡ ቆፍ ብሂል ቅሩብ እግዚአብሔር እግዚአብሔር ለልበ ቅኖችና ለየዋሃኖች ቅርብ የሆነ አምላክ ነው ማለት ነው። 20. ሬስ፡ ሬስ ብሂል ርኡስ እግዚአብሔር እግዚአብሔር ክብሩ ከእርሱ ለእርሱ የተገኘ የሁሉ ጌታ በሁሉ የሰለጠነ ነው ማለት ነው። 21. ሳን፡ ሳን ብሂል ስቡሕ እግዚአብሔር እግዚአብሔር በሥራው ሁሉ የተመሠገነ ነው ማለት ነው። 22. ታው፡ ታው ብሂል ትጉህ እግዚአብሔር እግዚአብሔር እንቅልፍ የሌለበት ትጉህ፤ ድካም የማይሰማው ጽኑዕ የሆነ ፈጣሪ ነው ማለት ነው።
Apr 19, 2022መዝ 118 ላይ የሚገኙት ናቸው ስሞቹ። በ22 ስነፍጥረታት ልክ ናቸው። እኚህ ስሞች አስቀድሞ አዳም በገነት እያለ ይጠራቸው ይጸልይባቸው የነበሩ ሲሆን ከገነት ከተባረረ በኋላ ይኅ ተሰውሮታል ለአዳም 7ተኛ ትውልድ ለሄኖክ ተከስተውለታል። ትንጓሜያቸውን ከዛው ከዳዊት ላይ ታገኛለህ።
Apr 19, 2022አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ ኃያል ሕያው አዶናይ ጸባኦት ኤልሻዳይ ያሕዌ አማኑኤል እብኖዲ ታኦስ ማስያስ ትስቡጣ ታዳኤል ኢያኤል ኢየሱስ ክርስቶስ Yemakachw enezn nw tirgum gn hulunm alakewm
Apr 19, 2022