አረ መላ በሉኝ ዘመድ ወዳጆቼ....😒 ሰላም🙌.... ከ 4አመት በፊት ነበር ጓደኞቼ እኔን በልጅቷ መፎገር የጀመሩት እና እንደ ቀልድ ነበር ለጊዜው እኔም ፉገራቸውን የምወስደው የነበረው... እና ከጊዜ በኋላ ለሷ ያለኝ ስሜት እየተቀየረ መጣ ሳያት ምን እንደሆነ ባላቅም እደነግጣለሁ እና ደሞ እሷን ለማየት የማላረገው ነገር የለም... እሷ ደሞ በተቃራኒው ለሁሉም ወንዶች ያላት ስሜት ተመሳሳይ ነው ከሁሉም ጋር ትቃለዳለች ትላፋለች(😡) እና በሩቁ እሷ ያላትን ስሜት ለማወቅ ያስቸግራል። በርግጥ የሆነ ጊዜ ላይ በጣም ነበር አይን ለአይን የምንገጣጠመው በዛ ላይ ከጓደኞቼ ጋር በሚገናኙበት ጊዜም ስለኔ ትጠይቃቸዋለች (ሁለታችንም ጎበዝ ተማሪዎች ነን )....በነገራችን ላይ 4 አመት ሙሉ ሳውቃት ያወራንበት ጊዜ ከ4 አይዘልም እሱንም ለጥቂት ደቂቃዎች ....ከሰሞኑ ደሞ ምንም መረጋጋት አልቻልኩም በሄድኩበት ቦታ ሁሉ እሷ ነች በዛ ላይ ማጥናትም እያቃተኝ ነው እሷም ትምህርቷ ላይ ለማተኮር ብላ ይሁን ለምን እንደሆነ በማላቀው ሁኔታ እንደበፊቱ አታየኝም ስለኔም አትጠይቅም😒ጓደኞቼን ሳማክራቸው ጠይቃት ይሉኛል እኔ ደሞ እሷን ማየት እንጂ የሚያስደስተኝ ከሷ ጋር ፍቅረኛሞች ሆነን መጃጃል አልፈልግም በዛ ላይ ዘንድሮ ተፈታኝ ነን እና ምን ይሻለኛል?? ፍቅርስ ነው ወይ ኢሄ? ወይስ አትኩሮቷን ስለነፈገችኝ የመጣ የቅናት ስሜት ነው??
Apr 14, 2022ልክ ነው ትኩረት ስላልሰጠችህ ነው እንጂ ፍቅር አይደለም።እና ደሞ ስሜትህን መለየትህ በጣም አሪፍ ነው።በቃ relationship አትፈልግም እና እሱን ደሞ ታቃለህ።አንዳንዱ የራሱን ስሜት እንኳን ሳይለይ relationship ይጀምርና የሰውን ህይወት ያበላሻል። ስለዚህ እርሷን ለመርሳት ሞክር እና focus on your studies dude.
Apr 14, 2022