for ortodox ታቦት ምንድነው ? Ena ke andu wede andu megbatu tkmu mndnew briefly btasredugn des ylegnal
Apr 12, 2022➕➕ስለ ታቦት መፅሀፍ ቅዱስ ምን ይላል?➕➕ ቤተመቅደስን ቤተ መቅደስ የእግዚያብሄር ማደሪያ የሚያሰኘው የቃል ኪዳኑ ታቦት ነው::በሰው ፈቃድ የተደረገ ሳይሆን በራሱ በእግዚያብሄር ፈቃድ የሰው ልጅ ያደርገው ዘንድና እርሱን ያመልክበት ዘንድ የተሰጠ ነው::ይህም ሰውና እግዚያብሄር ይገናኙበት ዘንድ ነውና:: 👉ታቦት የፅላት መያዣ ሲሆን 👉 ፅላት ደግሞ ህጉ የተቀረፀበት ታቦቱ ውስጥ የሚኖር ነው ይህ በእግዚያብሄር ለዘላለም ቃል ኪዳን ይሆን ዘንድ ለህዝቡ ማምለኪያ በሙሴ አማካኝነት የተሰጠ ነው:: 👉ዘፀ 31:18 "እግዚያብሄርም ከሙሴ ጋር በሲና ተራራ የተናገረውን በፈፀመ ጊዜ በእግዚያብሄር ጣት የተፃፈባቸውን ከድንጋይ የሆኑ ሁለቱን የምስክር ፅላቶች ሰጠው::" ይህን የእግዚያብሄር ራል ስንመለከት ስለ ታቦት እውቀት ይኖረናል 1.ታቦቱ(ፅላቱ) የተሰጠበት ቦታ ደብረ ሲና 2. .ታቦቱ(ፅላቱ) የሰጠ እግዚያብሄር አምላክ 3. የተሰጠው ለሚያምኑ ሁሉ 4.የተቀበለው የ እግዚያብሄር ሰው ሊቀ ነብያት ሙሴ 5.ባዶ ሳይሆን በእግዚያብሄር የተፃፉ ትዕዛዛት 👇ለምን ሙሴ ሁለት ታቦት ብቻ ተሰጠው?👇 ምክንያቱም 1.በላዩ የተፃፈበት አስርቱ ትዕዛዛት በሁለት ስለሚከፈሉ እግዚያብሄርን መውደድና ስሙን መውደድ 2.ለሙሴ በሁለቱም እጅ እንዲበቀል አድርጎታል ይህም የእግዚያብሄርን ትዕዛዝ በሙሉ ልባችን መቀበል እንዳለብን የሚያሳዩ ነው:: ሊቀ ነቢያት ሙሴ በመጀመሪያ የተቀበለው የምስክር ፅላት በእስራኤል ኃጢያት ምክንያት ተሰብሯል ሌላ ታቦት ከየት መጣ ብለው መናፍቃን ይሟገታሉ ነገር ግን ወረድ ብለው ካነበቡት በምትኩ ሌላ ይሰራ ዘንድ እግዚያብሄር አዞታል:: 👉ዘፀ 34:1-4 ""እግዚያብሄርም ሙሴን አለው:-ሁለት ፅላቶች እንደበፊተኛው አድርገህ ጥረብ በሰበርካቸው በፊተኞቹ ፅላቶች የነበሩትን ቃሎች እፅፍባቸዋለሁ ነገም የተዘጋጀህ ሁን በማለዳም ወደ ሲና ወጠህ በዚያ በተራራው ራስ ላይ በፊቴ ቁም::ከአንተም ጋር ማንም ሰው አይውጣ በተራራውም ሁሉ ምንም አይታይ መንጎችና ከብቶችም በዚያ ተራራ ፊት አይሰማሩ::ሙሴም እንደፊተኞቹ አድርጎ ሁለት ድንጋዮችን ጠረበ : በነጋውም ማልዶ እግዚያብሄር እንዳዘዘው ወደ ሲና ተራራ ወጣ ሁለቱንም የድንጋይ ፅላቶች በእጅ ወሰደ""":: ☝️መናፍቃን ለሙሴ ከሆነ ታቦት እንዲቀርፅ ስልጣን የተሰጠው ለምን ዛሬ ይሰራል ብለው ይሟገታሉ..ነገር ግን እግዚያብሄር ከሙሴ ውጭ መስራት እንደሚችሉ ስልጣን ሰጥቷል 👉 ዘፀ 31:1-8"እግዚያብሄርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው እይ ከይሁዳ ነገድ የሚሆን የሆር የልጅ ልጅ የኡሪ ልጅ ባስልኤል "" ታቦትን እንዲያዘጋጅ ታዟል:::ዛሬም ተዋህዶ ይህን ህግ ይዛ ታቦትን ታዘጋጃለች:: 👇የታቦት ሀይል👇 👉በኢያሱ 3:15 እንደተፃፈ እስራኤል የዮርዳኖስ ወንዝ ሞልቶባቸው መሻገር ባቃታቸው ጊዜ እንዲህ ሆነ::""ታቦቶቹንም የተሸከሙት የካህናቱ እግሮች በውሀው ዳር ሲጠልቁ ከላይ የሚወርደው ውሀ ቆመ" 👉በእያሱ 6 ላይ ካህናቱ ታቦቱን ይዘው 7 ጊዜ ሲዞሩ ጠንካራ የነበረው በጦር ኃይል ሊፈርስ የማይችለው የእያሪኮ ግንብ በእግዚያብሄር ታቦት የተነሳ ወደቀ:: 👉መፅ ሳሙኤል 5 ፍልስጤማውያን የእግዚያብሄርን ታቦት ንቀው አቃለው ከጣኦት አንድ ነን ብለው ዳጎን ቤት ቢያስገቡት ታቦቱ ጣዖቱን ሰባበረው አደቀቀው:: 👉1ኛ ዜና 13:9 ዖዛ ስልጣነ ክህነት ሳይኖረው ታቦቱን በድፍረት ቢነካ ተቀጣ : ተሰበረ ::ታቦት የሚሸከመው ካህን ብቻ ነው ዲያቆን እንኳን የተቀመጠበትን መንበር መንካት አይችልም:: 👇 ታቦት በአዲስ ኪዳን👇 እግዚያብሄር ይህን ቅዱስ ማደሪያውን መገለጫውን ለሙሴ ሲሰጥ ጊዚያዊ ሳይሆን ዘላለማዊ ነው:: የሚገርመው ነገር ታቦት ራሱ በሰማይ እንዳለ ቅዱስ ቃሉ ይነግረናል:: 👉 ራዕ 11:19"የእግዚያብሄር መቅደስ ተከፈተ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ" ለዚያ ነበር እግዚያብሄር ለሙሴ የሰማይን መቅደስ ሚስጥር ገልፆ የምድሩንም በዚያ አምሳል እንዲራ ያዘዘው 👉ዘፀ 25:9" እኔ እንደማሳይህ ሁሉ እንደ ማደሪያውም ምሳሌ እንደ ዕቃውም ሁሉ ምሳሌ እንዲሁ ስሩት"":: ወንድሞቼ እህቶቼ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እውነተኛ መሆኗን በግልፅ ያሳያል.....ዛሬ መናፍቃን ታቦትን ጣኦት እያሉ ሲሰናከሉበትም እያየን ነው::ለዚህም 👉በ ዕብ 13:9""ልዩ ልዩ አይነት በሆነ እንግዳዊ ትምህርት አትወሰዱ"" የሚለውን ቃል በማስተዋል በእምነታችን እንፅና እግዚአብሄር ያፅናን::: ወሰብሀት ለእግዚያብሄር!! https://t.me/sratebetkrstyane
Apr 13, 2022