Eski le general know lege new muslim yehonachu eski sele ፆማችሁ asredun malete please siga tebelalachhu yibalal..ewnet new endihum sele solat .. Yebelte bentewawok arif new beye new Thankes
Apr 10, 2022የፆም ትክክለኛ ትርጉም ምንድነው? በእስልምና እይታ ፆም ማለት ፈጣሪ አላህ በቁጥር የተገደቡ ቀናትን እንድንፆም አዞናል። ይህም ፆም ከመንጋቱ አስቀድሞ ወይም የለሊቱ ክፍለ ጊዜ ሊያልቅ ሲል እንበላለን(ስሁር ይባላል) እስከ አመሻሽ 12:30 አካባቢ ድረስ ከማንኛውም ምግብ: መጠጥ: የባል እና የሚስት ግብረስጋ ግንኙነት: ሰውን ከማማት ከመስደብ: ሰው ጋር ከመጣላት እና ከመሳሰሉት ነገሮች ታቅቦ መዋል ነው። አዕምሯችንን አንድ ጥያቄ እንጠይቅ እስኪ ዛሬ ፆሜን ዋልኩኝ ብል ምን እያልኩ እንደሆነ። ሳልበላ ሳልጠጣ ዋልኩ ነው ወይስ እየመረጥኩ በላሁኝ ለማለት ነው?? ጉዳዩ የመምረጥ ከሆነ ከስጋውም ከቂቤውም ከወተቱም ለአመት የማያገኙ የደሃ ደሃ ሰዎች አሉ። እና እነዚህ ሰዎች እድሜያቸውን ሙሉ እየፆሙ ነዋ !!! በሌላ እይታ ደግሞ አንድ Vegeterian የሆነ ሰው እድሜውን ሁሉ የሚመገበው ይህን ከሆነ እድሜውን ሁሉ ፆም ላይ ነዋ?? በኢስላም ግን ፆም ሃብታምም ይሁን ደሃ በእኩል ሰዓት መብላትን ጀምረው ያቆማሉ። ፆምን የሚፈቱበት ምግብ መለያየቱ ደግሞ የፆሙ ችግር ሳይሆን የፈጣሪ ፀጋ ነው።
Apr 10, 2022