1'በማያሻማሁኔታ እየሱስ ጌታ መሆኑን የሚናገሩ ክፍሎች በበቂ ሁኔታ አሉ አይኔን ምን ያርገው ካላልን በስተቀር ለምሳሌ ዮሐንስ ወንጌል( ምዕ10-30)"እኔ እና አብ አንድ ነን" በማለት ተናግሮአል ዮሐ1-1 በመጀመሪያ ቃልነበረ ይሄም ቃል ሁሉንም ያስገኘ እንደነበረ የሆነውም ሁሉ በእርሱ እንደሆነ ከሆነውም አንዳች ያለእርሱ እንዳልሆነ ከተናገረ በኋላ ይህም ቃል ስጋ እንደሆነ በቁጥር 14ላይ ይናገራል በተጨማሪም ዮሐ17፥1-5በዚክፍል ደግሞ የምናገኘው የእየሱስን ፀሎት ነው፤ይህም"አሁንም አባት ሆይ አለም ሳይፈጠር ባንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አንተ በራስህ ዘንድ አክብረኝ"ብሏል አለም ሳይፈጠር በፊት እየሱስ ነበረ ማለትነው መኖር ብቻ ሳይሆን በክብር ነበር የነበረው ሌላው እየሱስን ጌታ እንደሆነ ከሚጠቁሙ ክፍሎች በፋጥረት አፈጣጠርላይ እርሱም ከአብ እኩል ድርሻ እንደነበረው የሚያሳዩ ክፍሎች ናቸው ዮሐ1-3 ቆላ1፥16-17 ዕብ 1፥2 በዙ መጥቀስ ይቻላል።ቃል በቃል እኔ ጌታ ነኝ የሚል ከሆነ የምንፈልገው እኔ ሰውነኝ የሚልም አናገኝም ስለዚ ሰው አይደለም ልንልነው? አይሆንም እየሱስ እራሱን የሰው ልጅ እያለ ይጠራ እንደነበር የእግዚአበብሄር ልጅም ነበር ለምን ይመስላችኋል በዮሐ8-58ለይ "እውነት እውነት እላችኋለው አብርሀም ሳይወለድ እኔ አለሁ"ሲል ሊወግሩት ተነሱ ተሰወረባቸውም ይላል ለምን ሊወግረሩት ተነሱ?
እየሱስ ነብይም ነበር ጌታም ነው ሊቀካህንም ነው። ነብይ ማለት ምን ማለትነው?
የሁለተኛው ጥያቄ የእየሱስን ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክነት ካለመገንዘብ የመነጨነው። እየሱስ ሰውነው አምላክም ነው።ስላሴ የሚለው ቃል ተርቱሊያን በተባለ ሰው ለመጀመርያ ጊዜ በክርስትና እምነት ውስጥ የተተነተነ ሲሆን180ዓም ገደማ ነው ይህ ማለት ግን ብሉኪዳን መፅሀፍ ውስጥ በጭላንጭል ይታይ የነበረው የእግዚአብሔር አንድነት እና ሶስትነት በአዲስ ኪዳን ውስጥ በግልጥ ተነገረን እንጂ በዘፍጥረት መፅሀፍ ውስጥ እግዚአብሔር በብዙ ቁጥር እንዳለው ሆኖ ተዘግቦ ይገኛል። ለምሳሌ (ዘፍ 3፥22)ከእኛ እንደ አንዱ ይላል እግዚ አብሔር አንድ ብቻ ቢሆን እኛ ማለት ባላስፈለገው ነበር
ሌላው በ(ዘፍ 11፥7)ኑ እንውረድ በማለት። ተናግሮአል። ሌላው የእየሱስን ሰው መሆን ወይም መወለድ አስገራሚ አስደናቂ ከሚያደርጉት ነገሮ መሃል 1,የእግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያለው ፍቅር የገለፀበት ሲሆን 2,የአምላክ ሰው መሆን 3,አዳም በሀጥያቱ ከእርሱጋረ ሀጥያተኛ ሲያደርገን እየሱስ ግን ሀጥያት ሳይኖርበት የኛን በደል በመሸከም የእርሱን ፅድቅ ሰጠን 4, ከአብጋርም አስታረቀን 5,አብን ያየው አንድስንኳ የለም በዕቅፉ ያለው አንድያ ልጁግን ተረከው(አብን ለማወቅ መንገዱ አንድና አንድ ነው ወልድን ማወቅ ፊሊጶስ አብን አሳየንና ይበቃናል ባለው ሰአት እየሱስ እንዲህ ሲል መለሰ እስከዛሬ ከእናንተጋሆኘ አላወከኝምን" እኔ ያየ አብን አየ"በአለም ላይ እግዚአብሔርን (አብን)ያየው የለም ወልድን ያወቀ አብን ያውቃል ወልድን ያላወቀ አብንም አያውቀውም።
በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ በተለያየጊዜ በእየሱስ መንነት ላይ ጥርጣሬን በመፍጠር የተሳሳተ ግንዛቤ ውስጥ የሰመጡ ብዙ ኑፋቄዎች ተነስተው ያውቃሉ እነዚህን ኑፋቄዎች ጠቅለል አድርገን እንመልከት ካልን በሶስት ከፈለን ማየት እንችላለን 1,እየሱስ ሰው በቻ ነው የሚልሲሆን አነዚህ እየሱስ እግዚአብሔር የተላከ ታላቅ የስነምግባር መምህር መሆኑን ቢያምኑም መለኮትነቱን ግን ይክዳሉ።2,እየሱስ አምላክ እንጂ ሰውአይደለም ባይናቸው። እነዚህ ሰዎች ከመጀመሪያው ሀሳብጋር በተገላቢጦሽ ሲሆኑ እየሱስ መንፈስ ነበር እንጂ እንደማንኛውም ሰው አካል አልነበረውም የሚሉ ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ የእየሱስ መንፈስ በስጋውስጥ ያደረ የእግዚ አብሔር መንፈስ ሲሆን የሰው መንፈስ አልነበረውም ባይናቸው እንዲያም ተባለ እንዲህ ሁለቱም ስህተት ነው (ዕብ2፥17-18) 3,እነዚ ደግሞ እየሱስ ከአብ የሚያንስ አምላክ ነው ይላሉ እንደዚህ የሚሉት አካል የሃጥያት ማደርያ በመሆኑ ትክክለኛው እና ፃድቁ ጌታ በዚህ አካል ውስጥ መሆን አይችልም።በመሆኑም እየሱስ ከአብ የተላከ እንጂ የሚተካከል አይደለም ደሞ እርሱ እራሱ አምላክ አይደለም ይላሉ።ለዚህም ማስረጃ እየሱስ አብ ከእኔ ይበልጣል ብሎ የተናገረውን ያቀርባሉ(ዮሐ14፥28)ነገርግን እየሱስ አብ ከእኔ ይበልጣል በማለት የተናገረው ትስብእታዊ ተልኮውን-ሰው የሆነበትንና ስጋም በሆነበት ሁኔታ ያለውን እሱነቱን አስመልክቶነው።በሌላ ቦታ እየሱስ" እኔ እና አብ አንድነን"በማለት ተናግሮአል (ዮሐ10፥3)እንደገናም "እኔን ያየ አብን አየ"በማለት ተነግሮአል( ዮሐ14፥9) በመጨረሻም አንድ ነገር ልበል መፅሀፍ ቅዱስን ስናነብ አጉል የጦጣዋ ብልጠት አያስፈልግም ልባችንን ዝቅ አድርገን እንቅረብ እላለው።100%እየሱስ ሰውነው
100%አምላክነው
እየሱስ ጌታ ነው።
እየሱስ ፍቅርነው ወደዚህ ፍቅር ይጠራችሗል ኑ እርሱ ሸክማችሁን ይወስዳል
ቀንበራችሁንም ይሰብራል ከሀጥያት ባርነት ነፃ ያወጣችኋል ኑ ኑ ኑ ኑ ኑ ወደፍቅር ኑ
Apr 11, 2022