ምንም እንኳ ፊልም የገሀዱ ዓለም ነጸብራቅ ነው ተብሎ ቢታሰብም በፊልሞቻችን ላይ የምንመለከተውን ፍቅር በገሀዱ ዓለም ላይ የማጣታችን ምክንያት ምን ይሆን ? ፍቅንስ ያጣነው ፍለጋችንን ከተሳሳተ ቦታ ስለጀመርን ይሆን ? እስኪ ፍቅረኛ ያላችሁ ሰዎች ፍቅርን በሰማችሁት እና በፊልም በምታዩት ልክ ትኖሩታላችሁ ? ልኩስ ምን ያህል ነው 😐
Apr 10, 2022ፊልም የገሀዱ አለም ነፀብራቅ ነው የሚለው Theory ነው። አንድ የትወና አርት ውስጥ የምማር ሰው የመጀመሪያ ቀን ላይ የሚማረው ይሄንን ነው። ቲዩሪ ደግሞ ተግባር ስትቀይረው ልሰራም ላይሰራም ይችላል። እኔ በበኩሌ ፊልሞች ላይ በተለይ አማርኛ ፊልሞች ላይ ጠቅላላ የገሀዱን አለም ነፀብራቅ ያሳያሉ ብዬ አላምንም ... በተወሰነ መልኩ የዝች አለም እውነታን ይዘው እዛ ላይ ሙሉ የራሳቸውን ideology & imagination ሀሳብ ነው የምጥሉብን እናም የምሳዩን ተፈጥሮን ሳይሆን እነሱ የፈለጉት ነው ለዛ ይመስለኛል የፊልሙን ፍቅር ገሀድ ሆኖ የማናየው
Apr 11, 2022