የሆነ ልጅ አለ በጣም የዋህ ነው እና ከ2012 ጀምሮ ከኔ ፍቅር እንደያዘው ይነግረኛል እኔ ሁሌ እንደቀልድ ነበር የማየው በጣም ካመረረብኝ ደግሞ ለማስቀየስ እሞክራለሁ እኔ እንደ ወንድሜ ነው የማይህ ልለው እልና ግን እንዳልጎዳው እፈራለሁ በዚህ አመት ግን ብዙ ሰዎች የእውነት እንደሚወደኝ እንደሚያስታውቅ እየነገሩኝ ነው ባለፈው ለታ ላናግረው ሞክሬ ነበር ግን ከዛ ለምንድን ነው የምትጠይኝ እኔ መወደድ አልችልም ምናምን ብሎ በሌላ መንገድ ቀየረው እኔ ለልጁ ምንም ስሜት የለኝም እና ደግሞ በጣም ከመጠን በላይ ደግ የሆነ ልጅ ነው ልጎዳው አልፈልግም በዚህ ሰዓት ፍቅር ምናምን እንደማልፈልግ የሚያውቅ ይመስለኛል ማለቴ ጓደኞች ስለሆንን ብዙ ጊዜ እናወራለን እኔ አሁን የምፈልገው ከልጁ መራቅ ነው ምክንያቱም አብሮኝ ከሆነ እንደማልፈልገው ልነግረው አልችልም ይሉንታ ይይዘኛል ስለዚህ ጠልቶኝ እንዲርቀኝ እፈልጋለሁእና አሁን ጥያቄዬ ልጁን ሳልጎዳው እንዴት እንዲጠላኝ ላርግ
Apr 09, 2022እኔ ለራስሽ እድል እንድትሰጭው ነው የምጠይቅሽ እንዳልሽው አይነት ሰው ከሆነ ብትርቅው ትልቅ ሰው እንዳጣሽ ቁጠሪው የፍቅር ስሜት በመላመድም ልመጣ ይችላል
Apr 10, 2022