እባካችሁ አትለፉኝ! አንድ የ65 አመት አዛውንት እና የ61 አመት እናት በፊት ከሚኖሩበት አዲስ አበባ ቤታቸውን በ1.2ሚሊዮን ብር ካርታ ስለሌለው ሸጡና ከአዲስ አበባ በ58 ኪ.ሜ ርቀት በምትገኝ ቦታ 200 ካሬ ላይ ያረፈ ባለ 4 ክፍል ቤት በ 800,000 ብር ገዝተው በቀራቸው 400,000 ብር አዲሱን ቤታቸውን አድሰው እየኖሩ 3 ወር እንኳን ሳይሞላቸው ቤቱን ይገባኛል የምትል መጀመሪያ የሸጠላቸው ሰውዬ ሚስት መጥታ የይገባኛል ጥያቄ አቀረበች ። ቤቱን ለመግዛት ሲዋዋሉ ግን የቤቱ ባለቤት የያላገባ ወረቀት ይዞ ማንም ከገዛችሁ በኋላ ቤቱን የይገባኛል ጥያቄ የሚያነሣባቹ ሰው የለም ብሎ ነበር ግዢውን ከፈፀመ በኋላ ወደ ክፍለሀገር የሄደው ። ሚስቱ ግን በፍርድ ቤት ተከራክራ አሸነፈች ተባለ ከሰውየው ልጅ እስከወለደች ድረስ ቤቱ ይገባታል የልጆቿ ማሳደጊያ ነው ተብሎ ተሰጣት እነዛ ሁለት አዛውንቶች ግን ዘመናቸውን ሙሉ የለፉበት ገንዘብ አጥተው በተጨማሪም የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ከሰሙ በኋላ በከፍተኛ የጤና መታወክ እስከ ፓራላይዝ እስከ መሆን ድረስ ደርሰው ከመጦሪያ ቤታቸው ተባረው አሁን እዛው አካባቢ 1 ክፍል ቤት ተከራይተው እየኖሩ ነው አሁን መጠየቅ የምፈልገው በፍርድ ቤቱ ውሳኔ ትስማማላቹ ? እነሱን ሊረዳ የሚችል ማንኛውንም ሀሳብ ካላቹ አደራችሁን? ስላበዛሁት ይቅርታ አድርጉልኝ🙏
Apr 08, 2022ይህን ያህል መዝቀጣችን ይህን ያህል መደደባችን ያሳዝናል 😭😭 .... በሴትየዋ አትፈርድም ልጆቿን ብላ ይሆናል ግን ሰውየውን እንደሽንኩርት ነበር መክተፍ 😭😭 ምንም ስለህጉ ማወቀው ነገር የለም ግን እ 😢 ... ሰውየው ግን ምንም አልተባለም? እሱ ተቀጥቶ ሰዎችን መመለስ አይቻልም? ስለሱ አጣራ እስኪ እፀልይላቸዋለው በቻልኩት 🙏
Apr 08, 2022