ለ ፕሮቴስታንት ወንድሞቼ እና እህቶቼ አንድ ጥያቄ አለኝ። እናንተ ለምንድን ነው በ አቋራጭ ለመክበር በአቋራጭ ለመዳን የምትጥሩት ለምንድን ነው። የእግዚአብሔር መንግስት እንዴት ተተኝቶ ጮማ እየተቆረጠ በቀላሉ ኢየሱስ ያድናል በሚል ብቻ ድሕነትን ለምን ትፈልጋላችሁ። በጣም ስለሚገርመኝ ነው። በዚሕ ቀን በራዕይ እንዲሕ ነግሮኝ በኔ በኩል ትድናለሕ ምናምን እያሉ ነብይ እምትሏቸው ግን የቅዱሳንን አማላጅነት ግን ትክዳላቹሕ። ቆይ ወንጌሉ በብዙ መከራ እና ፈተና ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንደምንገባ ነው እሚነግረን እናንተ ግን በአቋራጭ ድሕነትን ፍለጋ ለስንፈታቹህ ጥቅስ ፍለጋ መሯሯጥ ከምን የተነሳ ነው??? ሁሉንም ነገር በድክመታቹሕ ብቻ ለእናንተ እንዲመች እያደረጋቹህ ፆሙን ፀሎቱን ንስሃውን ምፅዋቱን ለምን ታጠፉታላቹህ???
Apr 07, 2022'በአቋራጭ ለመዳን' ያልከውን መንገድ መጽሐፍ ቅዱስ ብቸኛ መዳኛ መንገድ አድርጎ ያቀርበዋል። አንተ እየጠቀስክ ያለውን ለመዳን ስራ መስራት ያስፈልጋል የሚለውን አቋም ደግሞ ይሄው መጽሐፍ ቅዱስ 'ልዩ/ ስሁት ወንጌል' ይለዋል። (ወደ ኤፌሶን ሰዎች ምዕ. 2) ---------- 5፤ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥ . . . 8፤ ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ 9፤ #ማንም_እንዳይመካ_ከሥራ_አይደለም። ወደ እግዚአብሔር መንግስት ለመግባት አንተ በቂ አይደለም ያልከው 'ኢየሱስ ያድናል' ብቸኛ መንገድ ነው። " መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።" (የሐዋርያት ሥራ 4:12) በክርስቶስ ስራ እንዲሁ በማመን ከመዳን ይልቅ እኔም መስራት አለብኝ የምትል ከሆነ የክርስቶስ መሞት ትርጉሙ ምኑ ጋር ነው? " ጽድቅስ በሕግ በኩል ከሆነ እንኪያስ ክርስቶስ በከንቱ ሞተ። " (ወደ ገላትያ ሰዎች 2:21) ወንድሜ እኛን ከእግዚአብሔር የለየን ጉዳይ በመልካም ስራዎች እልባት ማግኘት የሚችል አይደለም። እግዚአብሔር የሚፈልገው የልጁን (የክርስቶስን) መልክ ማየት ነው ምክንያቱም ብቸኛ ኃጢአት የማይከሰው አካል እሱ ስለሆነ ለዚህም እሱን በማመን በኛ ፈንታ እሱ እንዲታይልን የህይወታችን ብቸኛ ጌታ ካላደረግነው ሁሉም ድካምህ ከንቱ ነው። " እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው። " (2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:21) እስራኤላውያንን ማየት ብቻ እኮ በቂ ነው እንደነሱ ህግ ላይ የሚያተኩር አልነበረም ግን ከክርስቶስ ተለይተዋል። ስለ ማማለድ ያነሳኸው ደግሞ ድሮም፣ አሁንም፣ ወደፊትም ወደ እግዚአብሔር በማንም በኩል መቅረብ አትችልም። ምናልባት መለመን በሚለው ትርጓሜ ሁሉም ሰው ስለሌላው መዳን መጸለይና መለመን ይችላል #ሁሉም_የዳነ_ሰው ነገር ግን ማንም ቢሆን በኛና በእግዚአብሔር መካከል መካከለኛ ሊሆን የሚበቃ የለም። ብቸኛው መካከለኛችን ከእግዚአብሔር ጋር የታረቅንበት መንገድ፣ እንዲሁም ዛሬም ድረስ በአብ ቀኝ ለኛ የሚታይልን ሊቀ ካህናታችን እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው። " አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው #መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ #ክርስቶስ #ኢየሱስ ነው፤" (1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:5) ይህን እውነት የሚቃወም የትኛውም ግለሰብም ይሁን የሀይማኖት አስተማሪ እንዲሁም ሃይማኖት ራሱ ቢሆን ከመዳን መንገድ በእጅጉ ስቷል። ለበለጠ መረዳት የዕብራውያንን እና የገላትያን መልእክቶች ማንበብ ይረዳል።
Apr 07, 2022