Selam sewech endet nachu zare ke enante mfelgew neger ale mn meselachu 12+1 negn malet placement bemetebeq lay ena wede gudayu sgeba yehone lj ale gorebet neger nen ena meqerareb mawrat yejemernew ke 20qen befit new snawera maninetu betam miweded ayinet new bcha abren endnhon teyeqegn negn feraw mkniatum esu Muslim ne orthodox nen ena lbe abreshiw hugni yilegnal chinqlate degmo ayihonm yilegnal kezi befit fqr yizogn ayawqm gn ehe fqr yihon plz amakrugn
Apr 05, 2022እኔ ሙስሊም ነኝ እሆቴ። የምመክርሽ ከሱ እንድትርቂ ነው። አስቢው እስኪ ትዳር ይዛችሁ ልጆችን አፍርታችሁ... ልጆቻችሁ የትኛውን እምነት ሊከተሉ ነው? ምናልባት "የፈለጉትን ይከተሉ" ትዪኝ ይሆናል። ግን እንዲህ በቀላሉ የሚመለስ አይሆንም። ብዙ መዘዝ አለው። አንቺም በሀይማኖትሽ እኔም በሀይማኖቴ ብሎ ፍቅር ዘፈን ላይ ብቻ ነው የሚሰራው! እመኚኝ። ከቤተሰቦቻችሁ የሚመጣባችሁን ጣጣ አስቢ። ሴቶች በባህሪያችሁ ፍቅር ነክ በሆኑ ነገሮች ልባችሁ ወዲያው ይሸነፋል። ወደድኩት ምናምን ከሚለው ስሜት ወጥተሽ በትክክል አስቢበት። ጊዜያዊ ስሜት ህይወታችሁን እንዲያበላሽ አትፍቀጂ። ልጁ ያንቺን እሺታ ነው እየጠበቀ ያለው። አልፈልግም በዪው። ወንድ ወንድ ነው ይቆርጥለታል። ሴት ግን ፀፀቱ ይከብዳታል። ይህ ነገር እኔም ያለፍኩበት ነገር ነው። ቢከብደኝም አልፈልግም በማለቴ ከአላስፈላጊ ፀፀት ተርፌያለሁ። ወንድ ብሆንም.. ካልሆነ እና የምትፈላለጉ ከሆነ ደግሞ ወይ ክርስቲያን አድርገሽው ወይ ሙስሊም ሆነሽ ተጋቡ። እሱም አስተማማኝ አይደለም። ምክንያቱም አንዳችሁን ለማግኘት በማሰብ እምነታችሁን ስለቀየራችሁ ስትገናኙ ወደነበራችሁበት የመመለስ እድላችሁ ሰፊ ነው። ሶ አስቢበት... ሀሳቤ ነውስ😁🤷🏽♂
Apr 06, 2022