Does anyone know someone who gives out loan with interest, it's urgent please direct me to that person.
Sep 07, 2020ናኖቬንቴ ናኖቬንቴ የቁስ አካል-ጥሬ ገንዘብ ግንኙነትን ያብራራ ጽህንሰ-ሀሳብ ሲሆን ቁስ ሀብት በልዩ አላማ መገልገያነት ሳይገደብ የማያቋርጥ የእሴት ልዉዉጥን ተግባራዊ ለማድረግ መቻል አለበት ብሎ ይሞግታል፡፡ ቁስ ሀብት ለልዩ አላማ መገልገያነት በጥሬ ገንዘብ አማካኝነት የዕሴት ልዉዉጥ ሂደትን አንድ ሙሉ ምዕራፍ ያጠናቀቀ ንብረት ነዉ፡፡ ቁስ ሀብት ልዩ አላማን ለመከወን በእሴት ልዉዉጥ ከአንዱ ወደ ሌላዉ የሚሸጋገር ሲሆን በተለምዶአዊ ተፈጥሮዉ የተገደበ የእሴት መገለጫ ያለዉ ነዉ፡፡ ቁስ ሀብት የተገደበ የእሴት ባህሪያቱን ሳይሽር፤ በቋሚነት ወይም በጊዜአዊነት የባለቤትነት ቦታዉን ሳያጣ ተዘዋዋሪ እና ጣምራ የእሴት ፍሬ እንዲኖረዉ ማድረግ የናኖቬንቴ ማዕከላዊ ሀሳብ ነዉ፡፡ ሰዎች በርካታ የግል ቁስ ሀብት ማለትም እንደ ሞባይል እና ላፕቶፕ ያለ ማናኛዉም የግል ንብረት ኖሯቸዉ ጥሬ ገንዘብ ሲቸገሩ ማየት የተለመደ ነዉ፡፡ አንድ ግለሰብ ገንዘብ ሊያወጣ የሚችል የተለያየ ንብረት እና ሀብት ኖሮት ጥሬ ገንዘብን በጊዬአዊነት መቸገሩ የቁስ ሀብት የባለጣምራ እሴትነት ቴክኒካዊ ችግር እንዳለ ይጠቁማል፡፡ ሰወች በተለያየ ጊዜ የሚያጋጥማቸዉን ጊዝያዊ ጎደሎ ለመሙላት ችግር ዉስጥ ሲገቡ ማየት የተለመደ ነዉ ለድንገተኛ ህክምና፤ለትምህርት ቤት ክፍያ፤ለጉዞ፤ለስጦታ ድንገት ገንዘብ ፈልገዉ ያጣሉ፡፡ ዳሩ ግን ግለሰቦቹ ገንዘብ ሊያወጣ የሚችል ብዙ አይነት ንብረት እና ቁሳቀሱስ ሊኖራቸዉ ይችላል፡፡ ናኖቬንቴ የተለያየ ንብረት ያለዉ ሰዉ ጥሬ ገንዘብ መቸገር የለበትም ብሎ ያምናል፡፡ ናኖቬንቴ ንብረት ወይም ቁስ ህብት ባለጣምራ እሴት ነዉ የሚል ፍልስፍናን ያራምዳል፡፡ ባለጣምራ እሴት ማለት ቁስ ሀብት ቁሳዊ ወይም ማቴሪያሊስቲክ ግልጋሎትን ከመስጠት በተጨማሪ ቅስፈታዊ ፍላጎትን ለሟሟላት የጥሬ ገንዘብ አስፈላጊነት ሲኖር ጥቅም መስጠት የሚችል ማለት ነዉ፡፡ ናኖቬንቴ ሰወች አስቸኳይ ገንዘብ ሲያስፈልጋቸዉ ያላቸዉን ስልክ፤ላፕቶፕ ወይም ሌሎችን እቃዎች በመጠቀም በ10ደቂቃ ዉስጥ የሚያስፍልጋቸዉን ገንዘብ እንዲያገኙ የሚረዳ አገልግሎትን ይሰጣል፡፡ ናኖቬንቴን ለየት የሚያደርገዉ ግን ሰወች እቃወቻቸዉን ገንዘብ ለማገኘት እንደሚጠቀሙ ሁሉ ያንኑ እቃቸዉን ሳይለወጥ እና ሳይቀየር በቀላሉ ገንዘባቸዉን ተጠቅመዉ መልሰዉ እንዲያገኙት ማስቻሉ ነዉ፡፡ በዚህም ንብረቶ ጥሬ ገንዘቦ፤ ጥሬ ገንዘቦ ንብረቶ ነዉ ይላል! ሰወች እቃቸዉን ተጠቅመዉ ባገኙት ገንዘብ ለአጭር ጊዜ ያጋጠማቸዉን ችግር ፈተዉ እስኪመለሱ ድረስ በአደራ ጠብቆ ያቆይላቸዉ እና በትቂት ጭማሪ የራሳቸውን እቃ መልሰዉ እንዲገዙት ያስችላቸዋል፡፡ @nanovente
Sep 08, 2020