የሆኑ መሪጌታ አሉ እና እኔ ያለሁበት ደብር ብቻ ሳይሆን አዲስ አበባ ውስጥም ይታወቃሉ እና ግን ጥያቄ የሆነብኝ ነገር መቅደስ ውስጥ አይገቡም ቅኔ ማኅሌቱ የራሳቸው እስከሚመስል ድረስ ይመረግዱታል እና ለምን ይመስላችኋል መቅደስ ውስጥ የማይገቡት(መቀደሻውውስጥ ) አፍርሰው ይሆናል ብላችሁ ታስባላችሁ ? ሀስባችሁን ንገሩኝ (ጓደኞቻቸው የሆኑ መሪጌቶች መቅደስ ውስጥ ይገባሉ) Thanks in advance.
Mar 31, 2022አንድ ታሪክ ልንገርህ መነኮሳት ትምህርት ለመማር ወደ አባ ዳንኤል ይሄዳሉ መነኮሳቱም በኢዮብ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈውን "ሰማይም በጌታ ፊት ንጹህ አይደለም" የሚለውን ነበር የጠየቁት ይህን ግዜ አባ ዳንኤል እንዲ ብሎ መለሰላቸው #ዛሬስ እንሆ መነኮሳት ኃጢያታቸውን ማሰብ ትተው ስለ ሰማይ ይመራመራሉ " በማለት ሰማይ ንጹህ ያልሆነው ከእግዚአብሔር ንጽህና አንፃር መሆኑን አስረዳቸው። ምን ልልህ ነው 1ደኛ ይህ አንይነቱን ጥያቄ እዚህ ቦታ መጠየቅህ አግባብነት የለውም 2ተኛ ምን አገባህ ? የራስህን ኃጢያት እያሰብክ የእግዚአብሔርን ቸርነት እያሰብ ሰማያዊ ሚስጥራትን እያሰብክ ግሩም ግብርከ እያለክ አትኖርም ? ይህ ለነፍስህ ምን ይጠቅማታል 🤔 አይገቡም አይደል ? መብታቸው ነው። አይገቡም አይደል ግዴታቸው ስላልሆነ በነጻ ፍቃዳቸው ነው። ትክክለኛ መልሱ ያለው መሪጌታው ጋር ነው ጠይቃቸው ልንሰጥህ የምንችለው ምክንያት #ሐሜት ይባላል። ይህ ደሞ ለነፍስ አይጠቅምም።
Apr 01, 2022