ሰላም ሰላም እንዴት ናችሁ እኔ ደህና ነኝ ፈጣሪ ይመስገን እንግዲህ ላስቸግራችሁ ነዉ ተቸገሩልኝ ... ስሜ ይኔ ይባላል የ12ተኛ ክፍል ተማሪ ነኝ በተጨማሪም ዩቲዩበር ነኝ ያዉ አዲስ ጀማሪ ዩቲዩበር ማለት ነዉ ይሄ ለመተዋወቅ ያህል ይበቃል ወደ ጉዳዬ ስገባ ደህና የሰዉነት አቋም እንድኖረኝ ፈልጋለሁ ማለትም ቁመተ 1.90 ነዉ በጣም ረዥም ነኝ የሚያስጠላዉ ነገር ደግሞ በጣም በጣም ቀጫጫ ነኝ አስቡት ቁመት እና ቅጥነት ... ብዙ ሰዉ በዚህ ቁመትህ ላይ ስፖርት ብትሰራ በጣም physically ታምራለህ ይሉኛል እኔ ግን በዚህ ቅጥነተ ላይ sport ተጨምሮ ከዚህ የበጣስኩ ቀጫጫ እንዳልሆን ብዬ የመስራቱም ዕቅድ የለኝም ... አሁን ደግሞ እዚህ መፍትሔ አላጣም ብዬ ከች ብያለሁ ስለዚህ እስቲ... 1ኛ physically የሚያምር አቋም እንድኖረኝ ምን ላድርግ 2ኛ ምን አይነት ምግብ ልብላ ያዉ ለተማሪ የምመጥን ኪሴን የማይጎዳ እባካችሁ አይታችሁ እንዳታልፉት እወዳችኋለሁ
Mar 31, 2022እዚ 3 ጉልቻ ትዳር አማካሪዎች አጂ bodybuilder የሉንም mtsm ✅ ያው ፕሮቲንሼክ አትጠቀም እንደሚወራው አይደለም ለውጡ በታናሽ ወንድሜ አይቼዋለው 5 ጨርሶ ወፍ 2ኪሎ ነው የጨመረው ስለዚህ ስጋ ደሞ ውድ ስለሆነ እሱን ሚተካ ወንድሜ ሲጠቀም ያየሁት አኩሪ አተር በብዛት ተመገብ ፣ እንቁላል ጥሬውን ጅው ፣ ምስር ፣ሙዝ ለውዝ እና አከር/ማማ ወተት ገዝተህ ፈጭተህ ድው ፣ እንቅልፍ በደንብ ተኛ ፣ ምግብ በፊት 1 እንጀራ ምትበላ ከሆነ አሁን 1.5 ምናምን ተመገብ ፣ ውሃ ጠጣ ፣ 🚩መጀመሪያ አካባቢ ቦርጭ ሚመስል ነገር ሊወጣብህ ይችላል ስብ እየተከማቸ ስለሆነ ነው ከዛ ወጥረህ በቀን 1 ጊዜ 50 ደቂቃ ስፓርት ብትሰራ ያ ስብ ይበተንና muscle build ታደርጋለህ 🙌 ኮካ ምናምን ጋዝ ነገር አቁም
Mar 31, 2022