Selam sewoch ምን መሰላቹ በጣም የደሃ ልጅ ነኝ እና ግን ምለብሰው ልብስ ግን እንደ ደሃ አይደለም ያው fashionableየሆኑ ልብሶችን ባለብስም ግን ይህን ያክል ግን አያስፎግርም። እናም በምለብሰው አላፍርም እና ግን ዘመድ ጋር ለእረፍት ምናምን ጋር ስሄድ ልብስ ይሰጡኛል, ጎረቤት የሆነ ነገር እንስጥሽ ብለው ሰፍ ብዬ ስጠብቅ የራሳቸውን ልብስ, ma classmates ቤታቸው ስሄድ ልብስ በቃ የትም የማውቃቸው ሰዎች ሁሉ ወደነሱ ስሄድ ያረጀ ልብሳቸውን ይሰጡኛል።አቃለው ግን ለክፋት አይደለም ሚሰጡኝ ግን እኔን ያ ነገራቸው እየጎዳኝ ነው።ምን አይተውብኝ ነው ሁሉም ልብስ የሚሰጡኝ እያልኩ በጣም እሳቀቃለው። ቆይ እናንተ ለሰው ልብስ እስከ መስጠት ሚያደርስ ምን ብታዩበት ነው
Mar 30, 2022ይሄ እኮ አቺን ከመደገፍ እዪው ለሌላ ልብስ ብር ምናምን ከምታወጪ ብለው ይሆናል፣ሴት ናት መዘነጥ አለባት ፣ ምናምን ከሚሉ ሃሳቡች፣ ከጎንሽ እንዳሉም ለማሳየት ይሆናል በቃ ደሃ ከሆንሽ ደሃ ነው እነሱ ስለሚያውቁ በአለባበስ አትሸውጂያቸውም ። ግን ይሄ ነገር ከደበረሽ እረ አሁን አለኝ እግዚአብሔር ይስጥልኝ ብለሽ መተው ፣ ወይም በቂ ካለሽ ተቀብለሽ ካንቺ የባሱ ደሃ ደሃዎች መስጠት ግን ❤️ ግን የኔ ውድ አንድ ነገር ልንገርሽ ከነገሮች ለመመሽ ምናምን አትሞክሪ እሺ ሌላ የተበላሸ መንገድ ይከትሻል ። ደሃ ከሆንሽ ድህነትሽን አምነሽ መቀበል አለብሽ ጠንክሮ በመማር እና በመስራት ይለወጣል ። በልብስ በአኳኋን ምናምን ለመሸፋፈን አትሞንሪ አትፎካከሪ ይሄ ኢትዮጵያዊነት ነው ያለው ለሌለው ካለው ከራሱ ይሰጣል ። ደሞ በልብስ አይባንኑም ካልሽ በእጅ ፣ በቆዳ ፣ በምትቀባቢው በብዙ ነገር ሰው ሊያውቅ ይችላል ።
Mar 31, 2022