ሰላም ቤተሰቦች የሰው ልጅ መገኛ የጥንት ስልጣኔ መጀመሪያ የምትባለው ሀገራችን ኢትዮጵያ በታሪኳ የሚገራርም ነገሮችን አሳልፋለች ነገር ግን የኛ ኑሮን እንደ ታሪካችን ገናናነት ሳስበው ምንአልባት ጥንት ከተባለውም ጀምሮ በውጪ ሀገር እርዳታ ስንረዳ ነበር ማለት ነው ለምሳሌ የምግብ አይነቶችም ይሁኑ የሌላ ሲረዱን ነበር ? ሲረዱን ካልነበረስ በምንስ ምክንያት ይሆን የተረጂነት ( ጥገኝነት ) ላይ የወደቅነው ምንም የጎደለን አይመስልም ምክንያቱም ከውጪ ሀገር የሚመጣው ነገር ሀገራችን ላይ ስለሚኖር ብቻ ይሄ ነው በሉኝ በአሳማኝ ሀሳብ::💚💛❤
Mar 30, 2022የእውነት ግን ኢትዮጵያዊያን(ከኔ ጭምር) እየተረዳችሁ ነው እንዴ የሚመስላችሁ🤔🤔 እውነት ስንዴ ምን ምን በእርዳታ ተሰጠ ሲባል የረዱን ነው የሚመስላችሁ🤔🤔 ከሆነ ተሳስታችኋል ከእግዚአብሔር በቀር ማንም ረድቶን አያውቅም!!! #ሌቦች_በሏቸው። የሚሰጡት እየወሰዱብን ላለው ማዘናጊያ ነው። ለምሳሌ አውሮፕላን በሰማይ ሲበር ሕፃናት ጭንቅላታቸውን ቀና አድርገው እጃቸውን አፋቸው ላይ ጭነው አባባባባባ እያሉ አውሮፕላኑን መሸኘት እንደለመዱና ከጨዋታቸው እንደሚዘናጉ ነው። እርዳታ/ሽወዳ ነው። ሌላው እርዳታ የሚለቱ መጥተው መጻሕፍቶቻችን ለሚመዘብሩበት ላሊበላን አክሱምን ሶፍ ዑመርን ዳሽንን ኮምኩመው ለሚራቀቁበት እውቀት እና መንፈሳዊ ግብዐት ተመጣጣኝ ክፍያ እንደማይከፍሉን ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ጥቁሮች አይበልጡንም በሚል እሳቤ የአባቶቻችንን ላብ እርዳታ በሚል ስም ለውጠው የሚሰጡህ። የገባህ ይገባሀል ያልተዋጠልህ የሆነ ቀን(በቅርቡ) እየመረረህ የምትውጠው ይሆናል። 1888 እምዬ እርዳታ ከፈጣሪ ሲሹ ድል አደረጉ። 1929 ጃንሆይ እርዳታ ከጄኔቫ ሲሹ ስንት ሰው አለቀ ? የሚረዳት ይቺን ሀገር እግዚአብሔር ብቻ ነው።
Mar 31, 2022