Hello Plz sele ማህፀን በር ካንሰር metakuten negerugne....i think im infected 😔
Mar 26, 2022#የማህፀን_በር_ካንሰር የማህፀን በር ካንሰር ማለት ወደ ማህፀን መግቢያ በር (የታችኛው የማህፀን ክፍል) ላይ የሚፈጠር ካንሰር ነው። • የማህፀን በር ካንሰር በሀገራችንም ሆነ በአለማችን በከፍተኛ ሁኔታ ሴቶችን የሚያጠቃ የካሰር አይነት ነው። በዚህ በ2019 ብቻ በዩናይትድ ስቴትስ ከ 17,170 በላይ ሴቶች ተጠቂ ሁነዋል። በሀገራችንም እጅግ ተሰራጭቷል። • የማህፀን በር ካንሰር ሲነሳ የሚታወሰው ሂውማን ፓፒሎማ(Human Papiloma) የሚባል ቫይረስ ነው። ምክናየቱም ለካሰሩ መከሰት ዋናውና ቀዳሚው ምክናየት ይህ ቫይረስ ስለሆነ ነው። ይሁን እንጅ የዚህን ቫይረስ ክትባት በመውሰድ በዚህ ቫይረስ የሚመጣውን ካንሰር ሙሉ ለሙሉ መከላከል ይቻላል። • የማህፀን በር ካንሰር ምልክቶች • የመጀመሪያ አካባቢ ብዙውን ጊዜ ምልክት አያሳይም። አልፎ አልፎ የዳሌ አጥንት ዙሪያ ያልተለመደ ስሜት ከመፍጠር ውጪ። በዚህ ጊዜ ወደ ጤና ተቆም መሄድና ምርመራ ማድረግ እጅግ ጠቃሚ መከላከያ መንገድ ነው። • ዋና ዋና ምልክቶች 1. በወር አበባ መሀል ደሜ መፍሰስ 2. ከግንኙነት በኋላ ደም መፍሰስ 3. ከእርጣት በኋላ ደም መፍሰስ 4. በግንኙነት ወቅት ህመምና መጥፎ ስሜት 5. መጥፎ ጠረን ያለው የብልት ፈሳሽ 6. ደም የቀላቀለ የብልት ፈሳሽ 7. የዳሌ አጥንት አካባቢ ህመም • የማህፀን በር ካንሰር አራት ደረጃዎች ሲኖሩት የመጀመሪያውንና ሁለተኛውን በአፍ በሚወሰድ ክኒን፡ በጨረር፡ በቀዶ ህክምና ወይም ከሶስቱ በሁለቱ ሙሉ ለሙሉ አክሞ ማዳን ይቻላል። • የማህፀን በር ካንሰር ምክናየቶች 1. ሂውማን ፓፒሎማ የሚባል ቫይረስ 2. ከብዙዎች ጋር ፆታዊ ግንኙነት ማድረግ 3. ለአቅመ ሂዋን ሳይደረስ ግንኙነት ማድረግ 4. ሲጋራ ማጤስ 5. በሽታ የመከላከል አቅም መቀነስ 6. የወሊድ መከላከያ እንክብል ለረጅም ጊዚ መጠቀም 7. የአባላዘር በሽታ መከላከያ መንገዶች • ክትባቱን መውሰድ • ቀድሞ ግንኙነት አለማድረግ • ከተለያዩ ሰዎች ጋር ግንኙነት አለማድረግ • አለማጤስ • ክትትል ማድረግ ባጠቃላይ የማህፀን በር ካንሰርን በቀላሉ መከላከል፡ መለየትና መታከም ይቻላል።
Mar 26, 2022