Selam ወንድሞቼ ከሰው ጋር ብዙም አልግባባም ማለት የቤት ልጅ ነኝ መሰለኝ ። እንዴት ላስተካክለው please በጣም አስጠልቶኛል እንዴት እንደማስተካክለው ንገሩኝ። ደግሞ ወንድ ነኝ
Mar 25, 2022ብሮ በተቻለህ ፍጥነት ከቤት ለመውጣት ሞክር።ለሴትም ነው ግን በተለይ ወንድ ልጅ ቤት በተቀመጠ ቁጥር ከሴቷ በእጥፍ ነው የራስ መተማመኑን የሚያጣው።እኔ ከተሞክሮዬ ነው የምነግርህ ለስምንት አመት የወንድም ያህል ይቀርበኝ የነበረ ጓደኛዬ ብሎ ብሎ ሲያቅተው ሊተወኝ ተገዷል እኔን ከሰው ለመቀላቀል ያልፈነቀለው ድንጋይ አልነበረም።ብዙ ጓደኞች ያሉትና እጅግ ተወዳጅ ቢሆንም በኔ ምክንያት የተወሰኑትን ለማጣት ሁሉ ተገዶ ነበር።ሰው የሌለበት ጫካ ድረስ ፈልጎኝ መጥቶ እየጎተተ ወደከተማ ይወስደኝ ነበር ሁላ።ክላስ ውስጥ በረፍት ሰአት ብቻዬን ስቀመጥ ጓደኞቹን ትቶ እኔን ወደክላስ ተመልሶ እየጎተተ ያስወጣኝ ነበር።ብቻ ለኔ ብዙ መከራ ያየ ወንድሜ የምለው ይሄ ጓደኛዬ እንኳን ሊለውጠኝ አልቻለም ነበር ። ምክንያቴ በአስተዳደግ ችግር የተነሳ ከሰው ተገልዬና በቤት ታፍኜ በመኖሬ ነው።እና በተቻለህ ፍጥነት ከቤት አምልጥ ወንድሜ።ምንም ስራና ምክንያት አትፈልግ እንዲሁ ዞረህ ግባ።ከዛ ሰው መቅረብ ተራ ነገር ይሆንልሀል
Mar 26, 2022