እርዱኝ! ሰላም ቤተሰብ እኔ የ11 ክፍል ተማሪ ነኝ እና ገና ለወደፊቱ የ12 ክፍል ፈተና ማለትም (Entrance) በጣም ፈርቻለሁ። በአሁን ሰአት አንድ የ11ኛ ክፍል ተማሪ ማወቅ ያለበትን እውቀት እኔ የለኝም። በተለይ የማትስ ትምህርት ምንም የማውቀው ነገር የለም ። በዚህ የተነሳ አሁን ላይ ማጥናት ስሞክር በቃ ቀኑ እንዳለቀ እና ሰአቱ እንዳለፈ ነው የሚሰማኝ አሁን ወይም ከዚህ በፊት ያለፋችሁ ተማሪዎች እንዴት ነው ጊዜያችሁን የተጠቀማችሁት ? እና ደሞ ከ9-12 ያለውንስ ትምህርት እንዴት ነው የማጠናው? ስላበዛሁባቹ ይቅርታ 🙏 ለምትሠጡኝ ምላሽ አመሠግናለሁ
Mar 22, 2022አረ እንዲህ መጃጃል የለም 11 ሆነህ ጊዜ አልቋል ትላለህ እንዴ ብራዘር በጣም ጊዜ አለህ... እና ከ9-12 የሚለውን እሳቤ ተወውና extreme የ11 እና 12 የውሉንም ሳብጀክት ወግመህ ማንበብና በየዓመቱ የወጡትን የentrance ጥያቄዎች ከዛው ላይ መስራት ነው ዋናው ነገር፤ የሞኝ ጭንቀት ሳይሆን የብልህ አርገው ማለት መጨነቅህ ጊዜህን በአግባቡ እንድትጠቀም ያግዝሃል ከአጉል ነገር እንድትጠበቅ ጊዜህብን እንዳታባክን።
Mar 22, 2022