ሰላም እንዴት ናችሁ እስኪ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ እኔ ከዚህ በፊት መጽሐፍ አንብቤ አላውቅም ነገር ግን ማንበብ እፈልጋለሁ እስኪ እናንተ ካነበባችሁት ውስጥ ስል ፍቅር አንድን ሰው ወደፊት ተስፋ እንዲኖረው እና በቃ ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል የሚለዉን አባባል የሚያሟላ የመጸሐፍ ስምና ዋጋዉን አንብባችሁት የተለወጣችሁበትን ጠቁሙኝ። ለትብብራችሁ አመሰግናለሁ🙏🙏
Mar 21, 2022ጀማሪ እንደመሆንህ ቀለል ከሚሉ መፅሓፍቶች ብትጀምር መልካም ነው። ለመግዛት የሚከብድህ ከሆነ በpdf የፈለከው መፅሐፍ አለልህ። አንተ ብቻ አንብብ እንጂ ሳታስበው ነው ተስፋ በውስጥህ ማበብ የሚጀምረው። ታዳ የጀማሪዎች ምን መሰለህ የሆነ መፅሐፍ አንብበው ሲጨርሱ በጣም ደስ ስለሚላቸው ካለዛ መፅሐፍ እና ደራሳ ውጭ ለኔ ምኔ ይላሉ። ይሆ ችግር እኔንም ያጋጠመኝ ነው። ብዙ እያነበብክ ስትመጣ ግን ሚዛናዊ እየሆንክ ትሄዳለህ። የንባብ ፍቅር እንዲያድርብህ በመጀመሪያ የይስማዐከ ወርቁ መፅሐፎችን አንብባቸው። ተከታታይ ናቸው። 👇👇👇 ዴርቶጋዳ👉ራማቶሓራ👉ዣንቶዣራ👉ዮራቶራድ👉ዮቶድ ከፈለካቸው ልልክልህ እችላለሁ. Inbox👇 @mohgenerous
Mar 22, 2022