እርግጥ ነው የሰው ልጅ የሚደሰትበት ነገር ሊያስፈልገው ይችላል ቤተሰብ፣ ጥሪት፣ ሚስት፣ ልጅ የሚባሉትን ማለቴ ነው። ግን እነኚህን የሚተኩ ነገሮች በህይወቱ ካገኘ ለምሳሌ መጽሐፍትን...ሳያገባ፣ ሳይወልድ የራሱን ኑሮ መኖር አይችልም? የሌላው ህይወት ውስጥ ሳይገባ በብቸኝነት የሚመሯት ህይወት ከመረጧት ፊቷን የምታዞር ናት? ህይወት ራሷ ባዘጋጀችልን መንገድ ብቻ ነው መጓዝ ያለብን?
Mar 20, 2022የሚቻል ይመስለኛል ግን ልብ ይጠይቃል ('courage')። የተለመደውን መድገም ይቀላል የራስን ፍላጎት መጠየቅ፣ ማወቅ እናም ለማድረግ መሞከር ግን ስራ አለው።
Mar 21, 2022