ሰላም እንዴት ናቹ ምን መሰላቹ ነገሩ አንድ የclass ልጅ አለች እና በጣም ነው የምንተያየው በተደጋጋሚ ታየኛለች እኔም እንደዛው ስለእሷ ማሰብ እየጀመርኩኝ ነው ቦታ ቀይሬ ሳያት እንካን የበፊት ቦታዬ በአይና ታየኝና ከሌለው ዞራ ትፈልጋለች እኔ ደግሞ ሲበዛ አይን አፋር ሰው ነኝ ሴት ልጅ ቀርቤ አላውቅም ምን ባደርግ ይሻላል ትላላቹ?
Mar 19, 2022እሷ መታ እንድታናግርህ ነው እንዴ የምጠብቀው ካዲያ👀....እሷም እኮ አይናፋር ትሆናለች ስለዚ አንተ በድፍረት ሄደህ ካልጠየካት እንዲሁ አይን ለአይን እየተሽኮረመማቹ መኖራቹ ነው....already መጀንጀን እንኳ አይጠበቅብህም በአይንህ ድባቅ አርገሀል የቀረህ ነገር ቢኖር ወሬ ማስጀመር ብቻ ነው ስለዚህ ወንድሜ እንደወንድ ልጅ ቆፍጠን በልና ሰላምታ እንኳን በአግባቡ ለመለዋወጥ ሞክር እራስህን አረጋግተህ ፈታ ብለህ አውራት እመነኝ ነገሮች እየተስተካከሉ ይመጣሉ...ነገር ግን አሁን ባለህበት ከቀጠልክ ምንም የሚለወጥ ነገር የለም ምንም ነገር ቢሆን እራስህ ማድረግ እየቻልክ ከሰዎች በፍፁም አጠብቅ! መልካም የፍቅር ጊዜ አይናፋሩ👀
Mar 20, 2022