if u google it You can get more information rstger than asking on this. @Bermel_Mouth_AAE
Mar 18, 2022if u google it You can get more information rstger than asking on this. @Bermel_Mouth_AAE
Mar 18, 2022"ባሏ ሰክሮም ይሁን በሆነ አጋጣሚ ሚስቱን ከደበደበ መጀመሪያ የተመታችው ሴት/ሚስት የድረሱልኝ ድምፅ ዕልልታን በሚመስል ዜማ ኤሌሌሌሌሌ እያለች ታሰማለች ። ወድያው ድምጿን የሰሙ ጎረቤቶች ደርሰውላት ከባሏ ያስጥሏታል ። ቀጥሎም ያስጣሏት ሴት ጎረቤቶች የተመታችውን ሚስት/ሴት ይዘው በየ ሰፈሩ እየዞሩ በቅድሙ የድረሱልኝ ዜማ ኤሌሌሌሌሌ እያሉ ድምፃቸውን ያሰማሉ ። ይሄን ድምፅ የሰማች ማንኛዋም ሴት መብቷን ለማስከበር ከቤት እየወጣች ሰልፉን መቀላቀል ይኖርባታል ። ድምፁን ሰምታ ነገር ግን አሻፈረኝ ብላ በሯን የዘጋች ሴት ከተገኘች ሰልፈኞቹ ቤቷ ድረስ በመግባት ይዘዋት ይወጡና "እንዴት ለመብትሽ በርሽን ትዘግያለሽ ፡ አንቺላይ ቢደርስ በሚወጡልሽ ሴቶች ላይ ለምን እንደዚህ ታደርጊያለሽ" ብለው ይገስጿታል ። ያቺ ሴትም ተፀፅታ ይቅርታ ጠይቃ ሰልፉን ትቀላቀላለች ። ላጠፋችው ቅጣት ደግሞ ሴቶቹ ቤቷ ውስጥ በመግባት ቅቤና ወተት ይወስዱባታል ። ሌላው ነገር ደግሞ ሰልፉን ለመቀላቀል ስትሄድ ባሏ ከከለከላት እሱም በገዳ ሥርዓት መሠረት ቅጣት ይቀበላል ። ሴቶቹ በየ መንደሩ እየዞሩ ሁሉንም የሰፈሩን ሴቶች "እከሊት ስትመታ አልሰማሽም ወይ ፡ እህታችን ጥቃት ሲደርስባት ዝም ትያለሽ ወይ...!" እያሉ ከሰበሰቡ በዋላ ወደ ተደበደበችው ሴት ቤት ተመልሰው በር ላይ ተቀምጠው የተለመደ ድምፃቸውን ያሰማሉ ። ኤሌሌሌሌሌሌ ...!!! ይሄን ጊዜ ድምፃቸውን የሰሙ የሰፈሩ አባገዳዎችና ሽማግሌዎች ዛፍ ስር ተሰብስበው ምንድነው የተፈጠረው እያሉ ይነጋገራሉ ። ቀጥለውም ችግሩ ወደ ተፈጠረበት ቤት ሄደው ከሴቶቹ መረጃ ይወስዳሉ ። በመረጃው መሠረትም ችግሩን አደረሰ የተባለው ግለሰብ ተፈልጎ ይጠራና ምን እንደ ተፈጠረ በግልጽ ያስረዳል ። ከዛን ከአባቶቹ ምክርና ተግሳጽ ይወስድና ሴቶቹ እንዲጠሩ ይደረጋል ። እነሱም ሴቷ ላይ የደረሰውን እያስረዱ ለመብታቸው ይሟገታሉ ። በስተመጨረሻም ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘው ባል ይቅርታ ጠይቆ የተፈረደበትን ካሳ ለሚስቱ ከፍሎ ፣ እንደ ማይደግመው ቃል ገብቶ ፣ ህብረተሰቡን አመስግኖ ፣ አብልቶ ፣ የእርቅ ሥርዓቱ ይፈፀማል ። ይህ በኦሮሞ ህዝብ ውስጥ የሚደረግ ከገዳ ሥርዓት ውስጥ አንዱ የሆነው ሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት የሚከላከልና የሚቃወም ፣ ቀጥሎም ሴቶች በራሳቸው የራሳቸውን መብት የሚያስከብሩበት መንገድ ነው" ✦✺ @Minteno ✺✦
Mar 19, 2022Simply it is the first Democratic system in the world
Mar 18, 2022It is hard to explain because it is yet considered as the most complex egalitarian ruling system in Africa. You can find books "Gada: Three Approaches to the Study of African Society" እና "OROMO DEMOCRACY: An Indigenous African Political System" which is written by Professor Asmerom Legesse.
Mar 19, 2022