ሰላም, ብዙ ጊዜ መጠየቅ የምፈልገው ጥያቄ ነበር ፤ እግዚአብሔር አምላክ እኛ እራሳችንን ከምንወደው በላይ እንደሚወደን እንዲሁም እንደሚያስብልን በቅዱስ መፅሃፍ ተፅፏል። ነገር ግን በፍርድ ቀን በእርሱ መንገድ ያልሄዱት ወደ ዘለዓለማዊ እሳት ይጣላሉ ፤ እና አይደለም ከራሳችን በላይ የሚወደን አምላክ እኛ የምንወልዳቸው ልጆች ምን ቢያጠፉ እና ስልጣኑ ቢኖረን ወደ ዘለዓለማዊ ስቃይ እንጥላቸዋለን? ቀራኒዮ ላይ የተከፈለንን የደም ዋጋ ዘንግቼ አይደለም ፣ አልያም እንዲሁ በሃጥያት ለምን አንኖርም አይደለም ፣ ነገር ግን ይሄ ነገር ሁሌም ጥያቄ ስለሚሆንብኝ ነው?
Mar 18, 2022በሰውኛ ቋንቋ ዲሞክራት አምላክ መሆኑን አንዘንጋ ምርጫ ቀርቦልናል ወይ መንግስተሰማያትን መውረስ አልያም ሲኦልን መውረስ ሲኦል ባለስልጣን አለው በሱ ስራ ጣልቃ አይገባም እኛ ሰዎች ግን የሰይጣንን ምክር ከፈፀምን እንዲሁም ሰይጣን ሰይጣን ካጫወተን ፍላጎታችንን ያከብርልናል ፈጣሪም እንዳንገባ ከፈለግን ንስሀ የሚባል ነገር አለ ምንም ስራ ምንም ይቅር ይልሀል ከዚህ በላይ መውደድ ምን አለ (እና እባካችሁ ፈጣሪን በዝች ምጢጢዬ ጭንቅላታችሁ አትገምግሙት ትልቅ ሀጥያት ነው)
Mar 18, 2022