Plssss urgent help me out Bzu gize yalbegnal even gelayen tatbe erasu gn no metfo teren Ahun gn 1 week honegn ye sewnete teren mulu bemulu tekeyrual😭 bibte lab lab sayhon emishetew erasu lela teren new mn yishalegnal lomi yihew ahun arge neber gn ababasew ere erdugnnn😭😭🙏🙏🙏🙏😢😢 for ur advices egzer ystlgn
Mar 15, 2022ከመጠን በላይ ማላብ / Hyperhidrosis / ላብ ምንድነው? ላብ ሰውነታችን ራሱን የሚያቀዘቅበት ተፈጥሯዊ መንገድ ነው። አብዛኛው ይህ ሁኔታ ተፈጥሯዊ እና የጤንነት ምልክት ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ግን ተደጋጋሚ እና የማያቋርጥ ላብ ይታይባቸዋል እና ይህ ሁኔታ በህክምና ቋንቋ ሃይፐርሃይድሮሲስ/Hyperhidrosis/ ይባላል፡፡ ሃይፐርሃይድሮሲስ/ከባድ ላብ/ በላብ ዕጢዎች የሚመረተው ላብ ሰውነት ራሱን ለማቀዝቀዝ ከሚፈልገው በላይ ነው፡፡ ይህ በሽታ በአብዛኛው መዳፍንና የእግር ስርን እና ብብትን ያጠቃል፡፡ ጥሩው ነገር ግን ይህንን ችግር ለማከም የተለያዩ ዘዴዎች መኖራ ቸው ነው አብዛኛው ሰው ከበድ ያለ የጉል በት ስራ ሲሰራ፣ ሞቃታማ ቦታ ሲሆን፣ ድንጋጤ ወይም ጭንቀት እና አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሲሆን ያልበዋል፡፡ ከባድ ላብ ሃይፐርሃይድሮሲስ ያለበት ሰው የላብ ሁኔታ ግን ከላይ ከተጠቀሰው በእጅጉ ከፍ ያለ ነው፡፡ የከባድ ላብ ዋና ዋና ምልክቶች ቶሎ ቶሎ መምጣቱ የሚታይ ከሚገባው በላይ የሆነ እና ብብትን የሚያበሰብስ ሲሆን ነው፡፡ ከሚገባው በላይ የሆነ የሚያስጨንቅ የላብ መኖር በ ተለይም በእግር ስር፣ በብብት፣ በራስ እና በፊት ላይ የሚታ ይ ሲሆን፣ የቆዳ ማጣበቅ ወይም ከእጅ መዳፍና ከእግር መር ገጫ ጠብ ጠብ የሚል ላብ ሲታይ ነው፡፡ ሃይፐርሃይድሮሲስ የሚለው ስያሜ የሚሰጠውን የተቸ ጋሪውን የዕለት ተዕለት ስራን የሚያደናቅፍ ከፍተኛ የላብ መ ጠን/ከባድ ላብ ሲኖር ነው፡፡ ይህ ክስተት ያለ ምንም በቂ ም ክንያት ቢያንስ በሳምንት አንድ ጊዜ ይታያል፡፡ ለእነዚህ ሰዎ ች ከባድ ላብ እጃቸው ያለማቋረጥ ስለሚረጥብ ስራ መስራትም ሆነ መዝናኛ ቦታ ራሳቸውን ማዝናናት ይሳናቸዋል፡፡ በዚህም ም ክንያት ከሰው ጋር ሲጨባበጡ በእጃቸው ላብ ምክንያት እ ና ሸሚዛቸው የላብ ቅርፅ ስለሚያሳይ አንዳንዴ ላቡ ጠረን ስለሚኖረው በዚህ በሚፈጠርባቸው መሸበር ራሳቸውን ከ ሰው ያገላሉ፡፡ እንደዚህ ያለ ችግር ያለበት ሰው ከተለመደው በላይ ድንት ከፍ ያለ ላብ ሲያይ፣ ላብ የዕለት ተዕለት ስራውን ሲያደ ናቅፍበት፣ እና የሌሊት ላብ ያለ በቂ ምክንያት ሲኖረው ሐኪ ም ጋር መቅረብ ይኖርበታል፡፡ የብርድ ላብ የታየበት ማንኛ ውም ሰው ሐኪም ዘንድ መቅረብ አለበት፡፡ በተለይም ደግ ሞ ሁኔታው ከጭንቅላት ቅል መቅለል እና የደረት ወይም የ ሆድ ህመም ስሜት ጋር አብሮ ከመጣ የልብ በሽታ፣ የጭንቀ ት ወይም የሌላ ከፍተኛ ህመም ምልክት ሊሆን ስለሚችል ጊ ዜ ሊሰጠው አይገባም፡፡ የከባድ ላብ ምንጩ ሰውነታችን ሙቀቱን ከሚቆጣጠርበት የቁጥጥር ስርዓት ይመነጫል በተለይ ደግሞ የላብ ዕጢዎች ቆዳችን ሁለት አይነት የላብ ዕጢዎች አሉት፡፡ አንደኛው ኢክራይን ዕጢ ሲባል ሌላኛው ደግሞ አፓክራይን ዕጢ ሲባል ሌላኛ ው ደግሞ አፓክራይን ዕጢዎች ይባላሉ፡፡ ኢክራይን ዕጢዎች በአብ ዛኛው ሰውነታችን ውስጥ ሲገኙ በቀጥታ አፋቸው ወደ ቆዳ ላይኛው ክፍል ይከፈታል፡፡ አፓክራይን ዕጢዎች ግን የሚገኙት በብዛት ፀጉር በሚሸፍናቸው የቆዳ ክፍሎች ላይ ነው፡፡ ለምሳሌ የራስ ቅል፣ ብብት እና ጭገር አካባቢ ነው፡፡ የሰውነታችን ሙቀት ሲጨምር አውቶኖሚክ ነርቨስ ሲስተም የ ተባለው የአዕምሮ ክፍል እነዚህን ዕጢዎች ላብ ወደ ቆዳ የላይኛው ክፍል እንዲለቁ ያደርጋል፡፡ ላቡም ሰውነታችንን ከቀዘቀዘ በኋላ ይ ተንና ቆዳችን ይደርቃል፡፡ ይህ ላብ በውስጡ በአብዛኛው ውሃ እ ና ጨው ይይዛል አልፎ አልፎ ደግሞ ሌሎች ኬሚካሎችም በተጨ ማሪ ይይዛል፡፡ ከባድ ላብ በአንድ ቦታ የተወሰነ ወይም ጠቅላላ ወይም በርካታ ሰውነታችንን የሚያካትት /generalized hyperhidrosis/ በመባል ይከፋፈላል፡፡ የመዳፍና የእግር ከባድ ላብ በአብዛኛው ቀን ቀን የሚ ከሰት ነው፡፡ አንዳንዴም በብብት አካባቢም ይታያል በሁለቱም የሰውነታችን ክፍል በእኩል መልኩ ይታያል፡፡ ይህ አይነት ከባድ ላብ ወደ ሃያው የዕድሜ ክልል አካባቢ በአብዛኛው ይጀምራል፡፡ ከሌላ በሽታ ጋር ግንኙነት የሌለውና ራሱን የቻለ ችግር ነው፡፡ በርካታ የሰውነት ክፍልን የሚያጠቃው የከባድ ላብ ችግር አይነት በድንገት የሚጀምር ነው፡፡ በርካታ የሰውነት ክፍልን ያጠቃል፡፡ በ አብዛኛው ሌላ ምክንያት አለው፡፡ ለምሳሌ የመድሃኒት የጎንዮሽ ጉዳ ት፣ የበሽታ ምልክት፣ የማረጥ ምልክት፣ የስኳር መጠን በደም ውስጥ ዝቅ ማለት፣ የታይሮይድ በሽታ፣ የደም ካንሰር በሽታ፣ የልብ ድካም በሽታ ወይም የአንድ ወይም የሌላ ኢንፌክሽን በሽታ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ አስፈላጊውን መድሃኒት በመውሰድ ወይም መንስኤውን በሽታ በማከም ላቡን ያጠፋዋል፡፡
Mar 16, 2022