2012 ነበር 12th class ፈተና የወሰድኩት ግን አልመጣልኝም እንደገና 2013 Private ተፈትኜ ነበር ግን አልመጣልኝም ኮሌጅ ደግሞ ከፍዬ መማር አልችልም ለዚህ ነበር private የተፈተንኩት ግን አልሆነም😔 በቃ በራሴ ተስፋ እየቆረጥኩ ነዉ በየድርጅቱ እየሄድኩ ቅጠሩኝ ብዬ ለመንኩ ምናልባት ለኮሌጅ ክፍያ የሚሆን ካገኘዉ ብዬ መጥፋት እንዳለብኝ ይሰማኛል ግን የት መሄድ እንዳለብኝ አላዉቅም የሚሰማኝን ስሜት እንዴት መግለፅ እንዳለብኝ አላዉቅም😔 ግን በቃ ምን ላርግ የወንድምነት ሀሳባችሁን ለግሱኝ
Mar 15, 2022አይዞኝ ወንድሜ እስኪያልፍ ያለፋል። ያለህበት ቦታ ኢንደስትሪ ፖርክ ምናምን ካለ እዛ ስራ አይጠፋም እንዴትም ብለህ ሞክር ሀዋሳ ከሆንክ ልረዳህ እችላለዉ። ካልሆነም የቴክኒክ እና ሙያንም ዘርፍ እንደ አማራጭ ያዝ።
Mar 15, 2022