አሁን ያለው ፍልስፍና የሀሳብ ታሪክ ‹ድህረ ዘመናዊነት› የሚባለው ነው (ይሉናል)። የዚህ እሳቤ አንዱ መርህ “ሁሉም ነገር አንፃራዊ ነው።” በሚል ሽፋን የተጋረደ ነው። ይህን እሳቤ ከስብእና አንፃር እንዴት ታዩታላችሁ? …የምእራባውያን የትምህርት ስርዓት ‹ዝግመተ ለውጥን› እንደ እውነት ተቀብሎ እያስተማሩት መሆኑን ይነገራል። ‘ውሸት ስትደጋገም እውነት ትመስላለች!’ እንደሚባለው ሁሉ ዝግመተ ለውጥም እንደ እውነት ተቆጥሮ፣ በትምህርቱ ይሰጣል ማለት ነው። በ'ርግጥ ‘ዝግመተ ለውጥ እውነትም፣ ውሸትም ነው’ የሚል ጥልቅ ምንባብ የለኝም፤ …ግን በውስጡ ብዙ ክፍተት'ና ያልተመለስሱ ጥያቄወች እንዳሉት አውቃለሁ። ሲቀጥል መላምት ብቻ ነው። ይሄ ትምህርት ፈጣሪን ስለሚገድል “ስብእና በሰው ልጆች የተፈጠረች ናት።” የሚል ድምዳሜ ላይ ያደርሰናል። ይህ ሀሳብ አሁንም “አንፃራዊነት’’ ላይ ያስቀምጠናል። …ይሄ እሳቤ ምእራባውያኑ የአምላክን መሞት እሙን አድርገው የስብእና መሰረት፣ ልክ ኒቼ እንዳለው ‹የሀይል ፈቃድ (will to power)› ላይ መገንባት አለበት እያሉ ቢሆንስ? ይህ እሳቤ ሀያላን ሀገሮች (ምእራባውያን) ብርታት የሚሰጣቸው አይመስላችሁም? ሲጠቃለል፥ የምእራባውያኑ የስብእና መንፈስ ወደሄት እየሄደ ነው፤ ብላችሁ ታስባላችሁ? ሀሳባችሁን ስጡበት!
Mar 13, 2022Aytekemem aygodam bemilew new ene mayew bnawkew chgr yelewm mawek tru new banakewm degmo chgr yelewm wanaw sebiena newna gn meirabyawyanu yehiwetachn akal endihon adrgewtal ahun lay
Mar 13, 2022