Hello guys I can write an amazing film scripts n wanna sell them.but I have no contact help me.
Aug 23, 2020👉🏽ወረቀትና እስክሪብቶ + ሀሳብ አላችሁ? ተወዳደሩና 5000 ብር ተሸለሙ 🔥🔥 መቼም አወዳድሮ በመሸለም አልታማም አይደል? ዛሬም ብዙዎቻችሁን የሚያሳትፍና የሚያሸልም ውድድር አዘጋጅቼላችኃለሁ!! እንዴት ናችሁ ግን ቤተሰብ?ተጠፋፋን አይደል? አዲስ ዩቱዩበር ቀልብ የለውም 😜 ወደ ገደለው ስንገባ ይህ ውድድር የተዘጋጀው በመሰረታዊነት አዲስ የከፈትኩትን የዩቱዩብ ቻናሌን ለማስተዋወቅ ነው:: እየመጣሁ ሰብስክራይብ አድርጉ እያልኩ በባዶ ከማዝጋችሁ እናንተንም ለማሳተፍ በማሰብ ማለት ነው:: በቀጣይነት ግን ምርጥ ሀሳብ እና የመፃፍ ብቃት ላላችሁ ልጆች ስራችሁን እንድታወጡ በዛውም እንድትሸለሙ ለማገዝም ነው:: ውድድሩ ከ8 እስከ 10 ደቂቃ የሚወጣው የድራማ ስክሪፕት መፃፍ ነው:: ይህን ካልን ዘንዳ ወደ ውድድሩ ይዘትና መስፈርት ዘው እንበል:: ለመወዳደር የሚጠበቅባችሁ መስፈርቶች ..... 1. ያው ምን ሊሆን ይችላል? ቻናሌን ሰብስክራይብ ማድረግ ነዋ!! 2. ሀሙስ ሀሙስ እያቀረብኳቸው ያሉትን አጭር ቪዲዮዎች መመልከት!! ምክንያቱም የምትወዳደሩበት ስክሪፕት ከነዚህ ድራማዎች ጋር ተመሳሳይ ቅርፅ ሊኖረው ይገባል:: ያ ማለት በሃሳብ አይደለም:: ለመወያየት መነሻ የሚሆን ወይም ሊተኮርበት የሚገባ የህይወት ክፍል ነው የምትሉትን ነጥብ የያዘ መሆን አለበት ለማለት ነው:: እንዲቀልላችሁ ቪዲዮዎቹን ብታዩ 100% ይመከራል:: በቃ .... ርዕስ ... ሀሳብ .., ገደብ የለውም!!!! መፃፍ ነው!!! ከአንድ እስከ ሶስት የወጡት ስክሪፕቶች ወደ ተሰርተው ለእይታ ይቀርባሉ:: ከዚህ በተጨማሪ ግን 1ኛ የወጣው 5000 ብር 2ኛ የወጣው 3000ብር 3ኛ የወጣው 2000 ብር ይሸለማሉ:: 👉🏽የውድድሩ ማብቂያ ቀን ሳይጨምር ሳይቀንስ ነሀሴ 30 ነው:: 👉🏽 ከአንድ እስከ ሶስት ከሚወጡት ፅሁፎች በተጨማሪ ሀሳቡን የወደድኩትና ስው ጋር ቢደርስ ያልኩትን እያስፈቀድኩ የምሰራው ይሆናል:: 👉🏽ፅሁፎቻችሁን @merifeleke በሚለው የቴሌግራም አድራሻ አስገቡ!! 👉🏽እባካችሁ እውነት ነው ወይ ምናምን የሚል ጥያቄ እረፋ .... እንኳን ለገንዘብ ለነፍስ እታመናለሁ ... ከፈለጋችሁ ነፍሳችሁን አደራ ሰጥታችሁኝ ሞክሩት😜 መልካም እድል!! የዩቱብ ቻናሌ የሚከተለው ነው!! https://www.youtube.com/channel/UCI438EvFqBmrNo5uFXYx_0Q @yemeri_terekoch
Aug 23, 2020