#religion ዩኒቨርሲቲ ላይ የክርስቲያን በዓል ሲሆን " እንኳን አደረሳቹ " አትበሉ ምትሉ ሙስሊሞች እንደት ነው ክርስቲያን ያለበት ሀገር እየኖራቹ ያላቹት?
Mar 09, 2022ዋና ሀሳብክ ባይገባኝም ጥሩ ጥያቄ ነው....እና ደግሞ ይህ በ ዩንቨርሲቲ ብቻ አይደለም ሀይማኖታችን ስለ መቻቻል እና መከባበር በደንብ ያስተምራል ሚተገብረው ግን ጥቂቱ ሠው ብቻ ነው። የእስልምና ተከታይ ከ ክርስትያንም፣ከ ፕሮቴስታንትም፣የሁዳም ብቻ ከማንኛውም እምነት ተከታይ ጋር አይደለም በ ሀገር በ አንድ ጣሪያ ውሰጥ አብሮ ሊኖር ማህበራዊ ህይወቱንም ሊያስቀጥል ይችላል፤ደስታ ሀዘኑንም ሃይማኖቱ በሚያዘው መልኩ ይካፈላል። በቅዱስ ቁርዓን እንዲህ የሚል የ ፈጣሪ አሏህ ቃል አለ لَكُمْ دِينُكُمْ وَلِيَ دِين}] «ለእናንተ ሃይማኖታችሁ አልላችሁ፡፡ ለእኔም ሃይማኖቴ አለኝ፡፡}] 6:119 ሌላው ህብረተሰብ ደስታዬ ወይም በዓሌ ብሎ የያዘው ከራሱ ሃይማኖት አስተምርሆ ጋር ሚጋጭ ከሆነ ያለምንም አማራጭ ከመተግበር ወደኋላ ይላል ለምሳሌ ክርስትያኑ እየሱስ ተሰቀለ (ወይም ፈጣሪያችን ተወለደ ብሎ የሚያከብረውን በዓል ሙስሊሙ በቅዱስ ቁርዓን 3:112 لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ}] «አልወለደም፤ አልተወለደምም፡፡]} በሚለው መሠረት ጌታ አልተወለደም ብሎ እያመነ ሳለ ለ ሌላው ህብረተሰብ በመቻቻል በማህበራዊ ግብብነት ወይም በሌላ ምክንያት አሳቦ ይህን ሰው ለ ደስታው እንኳን ደስ አለክ ማለት አለብኝ ካለ ተሳስቷል። ምክንያቱም ሀይማኖቱ ይህን አያዝም...ነገ እንደ ሚሞት እና ፈጣሪ ፊት በሰራው ጥፋት እንደሚጠየቅ የሚያውቅ ሙስሊም ለአንድ ቀን ደስታ በ ጉርብትና በማህበራዊ ኑሮነት ምናምን አሳቦ ፈጣሪውን ሊያስቆጣ እኔ ነብይ ነው ምለውን እየሱስ(ዒሳ) እናንተ ጌታችን ነው ስላላችሁ ፣ ተወለደልን ስላላችሁ፣ተሰቀለልን ስላላችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ደስታችሁ ለኛም ደስታ ነው ልንል አይገባም። «ለእናንተ ሃይማኖታችሁ አልላችሁ፡፡ ለእኔም ሃይማኖቴ አለኝ፡፡ ሀይማኖት ነክ ባልሆኑ ሌሎች ማህበራዊ ጉዳዬች ግን ደስታ ብንለዋወጥ ግን አይከፋም (እንኳን በሰላም ትምህርትክን/ሽን ጨረሽ እንኳን ሚስት/ባል አገባክ/አገባሽ ሌላም ሌላም....
Mar 09, 2022