1,የኦርቶዶክስ እና የካቶሊክ ሀይማኖቶች ምንድን ነው ልዮነቱ ? 2,እና ስለ ፍቅር ግንኙነት ህጋቸው ምንድ ነው? 3,የአብይ ፆምን ይፆማሉ?
Mar 09, 20221) ብዙ ልዩነቶች ይኖራሉ ግን ጥንስስ ልዩነቱ የክርስቶስ የተዋሕዶ ሚስጥር ስለመቀበል እና አለመቀበል ነው። ኦሮቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከሁለት እካል አንድ የተዋሐደ አካል፤ ከ2 ባሕርይ አንድ የተዋሐደ ባሕርይ ስትል፥ የካቶሊክ ቤ/ክ ደሞ 2 አካል አንድ የተጨፈለቀ ባሕርይ የሚል እምነት አላቸው። There are so many differences then after but ትልቁ ልዩነት ይህ ነው። 2) ኦሮቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አባል የሆነ ሰው በሃይማኖት ከማይመስለው ጋር መጋባትም ሆነ ወደነሱ መቅደስ ገብቶ ቁርባናቸውን መካፈል አይችልም። በካቶሊክ ዘንድ ደሞ በአቅራቢያ የካቶሊክ ቤ/ክ ከሌለ ከግሪክ ቤተክርስቲያን ቁርባን መውሰድ እንደ ሁኔታው ይፈቀዳል። ከዚም በተጨማሪ የፓፑ መልካም ፈቃድ ወሳኝ እንደመሆኑ ካቶሊክ ካልሆነ ሰው ጋር መጋባት context-based ነው። በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቀኖና ዘንድ ግን በየትኛውም ሁኔታ አይፈቀድም፥ ከተጋቡ በኋላ በሃይማኖት ስለተለያዩ ብላም አታፋታም። 3- አዎ ይጾማሉ ግን ከኦርቶዶክስ ተዋህዶም ሆነ ከግሪክ ኦሮቶዶክስ ቤ/ክ የተለየ ነው። የጾም ካለንደራቸው እንደ ኦሮቶዶክስ የኒቂያን አዋጅ አይከተልም። የቀን ልዩነትም አላቸው።
Mar 09, 2022