selam sewoch sele ኑዛዜ ለምን ያስፈልጋል የቀኖና ጥድቅም yemiawera metsehaf ena tekumugn aschekuay new betam
Mar 05, 2022ንሰሐ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ 1 ንስሐ ማለት ምን ማለት ነው? ☞ ንስሐ ማለት፦ "ነሰሐ" ከሚል የግዕዝ ግስ የወጣ ቃል ነው፡፡የቃሉ ፍች ሐዘን፣ፀፀት፣ቁጭት፣ምላሽ፣መቀጮ፣ቅጣት ፣ቀኖና፣የኃጢአት ካሣ ማለት ነው፡፡ ንስሐ ማለት ደግሞ አንድ ሰው በሠራው ጥፋት፣ባደረገው ስህተት፣በፈጸመው ኃጢአት ማዘኑና መቆርቆሩን፣መፀፀቱን ዳግመኛም ያንን የመሰለ ኃጢአት ላለማድረግ የሚወሰነው ውሣኔ ነው፡፡ በአጠቃላይ ንስሐ ከፍ ብሎ የተገለጠውን ትርጉም ሲኖረው በሰዎች ሕይወት ውስጥ ደግሞ የሚከተሉትን ፍቺዎችን ይዞ እናገኘዋለን፡፡ ❖ ንስሐ ወደ እግዚአብሔር መመለስ ነው፡፡ ❖ ንስሐ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ ነው፡፡ ❖ ንስሐ ከኃጢአት እንቅልፍ መንቃት ነው፡፡ ❖ ንሰሐ ወደ መንፈሳዊ ሕይወት መመለስ ነው፡፡ ❖ ንስሐ ከእግዚአብሔር የሚሰጥ እግዚአብሔርን የሚያስወድድ ከንጹሕ ልብየሚመነጭ ጸጋ ነው፡፡ ❖ ንስሐ ከኃጢአትና ከዲያብሎስ ባርነት ነፃ መውጣት ነው፡፡ ❖ ንስሐ ስለእግዚአብሔር ፍቅርና ስለ ቅድስና ብሎ ኃጢአትን መተው ነው፡፡ ❖ ንስሐ ወደ መንግሥተ እግዚአብሔር የሚያስገባ ቁልፍ ነው፡፡ ❖ ንስሐ የመንግሥተ ሰማያት መግቢያ በር ነው፡፡ 2. የንስሐ ቅድመ ዝግጅቶች ምንላቸው ምን ምን ናቸው? ☞በአጥቢያችን ከሚገኝ ቤ/ክ ክህነት ያላቸው በአገልግሎት ላይ ያሉ መልካም መንፈሳዊ ምግባር ያለቸውን አባቶች መርጠን አበ ነፍስ(የንስሐ አባት) መያዝ ☞ የሰራነውን ኃጢአት ማመን ☞ በሰራነው ኃጢአት ከልብ አብዝተን መቆሮቆሮ መፀፀት ማዘንና ማልቀስ ☞ እግዚአብሔር ይቅር እንዲለን በፍጹም ትህትና ራስን በማዋረድ መጠየቅ ☞ በንስሐ ውስጥ መኖር የሚያሰጣቸውን የህሊና እረፍትና በረከት መገንዘብ ☞ ከእኛ ኃጢአት ይልቅ የእግዚአብሔር ቸርነትና ይቅር ባይነት እንደሚበልጥ እና ይቅር እንደሚለን ያለጥርጥር ፍጹም ማመን ☞ ወደ አበ ነፍሳችን ሄደን ንስሐ ለመግባት እና ቀኖናችን ለመቀበል ማሰብ እና መወሰን ☞ ከልጅነት እስከ ዕውቀት የሰራናቸውን ኃጢአቶች ማስታወስ ከተቻለም ለማስታወስ ይረዳን ዘንድ በጽሑፍ መያዝ ☞ ዳግም ወደ ሰራነው ኃጢአት እንደማንመለስ ለራሳችን ቃል መግባትና መወሰን፣ኃጢአትን መጸየፍ ☞ ወደ አበ ነፍሳችን ሄደን የሰራነውን ኃጢአት በሙሉ አንድም ሳያስቀሩ በዝርዝር መናዘዝ ☞ የሚሰጠንን ቀኖና ወይም ቅጣት በትክክል መተግበር ☞ ዳግም ወደ ኃጢአት እንዳንመለስ ራሳችንን በቃለ እግዚአብሔር ማነጽ 3. ኃጢአት ለንስሐ አባት መናዘዝ ለምን አስፈለገ? ☞ ስልጣነ ክህነት የማሰር የመፍታት ስልጣን ከእግዚአብሔር ስለተሰጣቸው፡፡ ማቴ.፲፰፥፲፰ " እውነት እላችኀለው በምድር የምታስሩት ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል፡በምድርም የምትፈቱት ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል" ☞ ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያዘዘው ትዕዛዝ ስለሆነ፡፡ ሉቃ.፭፥፲፬ "ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፡ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ስለመንጻትህ ሙሴ እንዳዘዘ መሥዋዕት አቅርብ አለው" ☞ ኑዛዜ ማድረግ በመጽሐፍ ስለታዘዘ፡፡ዘሌ.፭፥፭-፮፣፲ "ከእነዚህ ነገሮች በአንዲቱ በደለኛ ቢሆን የሠራው ኃጢአት ይናዘዛል፡ስለሠራው ኃጢአት ለእግዚአብሔር የበደልን መስዋዕት ያመጣል.....ካህኑ ስለኃጢአቱ ያስተሰርይለታል....እርሱም ይቅር ይባላል"፡፡ ☞ ከእኛ ይልቅ ለእግዚአብሔር ቅርብ ስለሆኑ እለት እለት እግዚአብሔርን በቅዳሴው ስለሚያመሰግኑ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን በየቀኑ እየፈተቱ ስለ እኛ ኃጢአት ይቅር እንዲለን ስለሚለምኑ፡፡ እግዚአብሔር ለንስሐ ፍሬ ያብቃችሁ @kedusgebreal @kedusgebreal @kedusgebreal
Mar 05, 2022