#ዳግማዊ አድዋ!💚💛❤💪 የካራ_ማራ_ጦርነት ( ኢትዮ - ሶማሌ ጦርነት ) የካቲት 26 / 1970 ዓ.ም " የኢትዮ-ሶማሊ ጦርነት ተብሎ የሚታወቀው የኦጋዴን ጦርነት ከሶማሌ ዲሞክራቲክ ሪፖብሊክ ጋር በ1969 ዓ.ም ተጀምሮ የካቲት 26/1970 ዓ.ም የተጠናቀቀው ጦርነት ነው፡፡ መጀመሪያ.በሶቪዬት ህብረት ቀጥሎም በ ዩናይትድ ስቴትስ ድጋፍ ኢትዮጵያን የወረረው የሰይድ ባሬ (ዚያድባሬ) ጦር ‹‹የእናት ሀገር ጥሪ›› እያለ ከመላው የኢትዮጵያ ምድር በተሰባበሰበ ጀግናው የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ድባቅ ተመታ፡፡ ዚያድ ባሬ የካቲት 26፣ 1970 ዓ.ም የኢትዮጵያን ምድር ዘልቆ በመውረሩ፣ የኢትዮጵያ ጦር በመልሶ ማጥቃት በአየርና በምድር # ካራማራ ተራራ ላይ ከባድ ውጊያ አካሄደ፡፡ የሶማሊያን የአየር ክልል ጭምር ዘልቆ በመግባት የኢትዮጵያ የጦር ጀቶች ማሰስና ማደባየት ቻሉ ። ዓለምም ጭምር ሶማሊያን ማገዝ አይደለም ስለ ሶማሊያ ነጋሪ እስኪጠፋው ወደመች ። የሶማሊያ ብሄራዊ ጦር ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ አደጋ ውስጥ ወደቀ ተራራዎቹ ሁሉ በምድር በካርቤል እና እና ቢየም ሮኬቶችና መካከለኛ ርቀት ተተኳሽ ሚሳዮሎች ከሰማይ ደግሞ የአውሮፕላን ሮኬቶችና ቦንቦች ካራማራ ተራራ ላይ ዶፍ ወረደባት ፤ ከምድር እሳተገሞራ የፈነዳባት መሰለች ። ከዚያም የኢትዮጵያ ጦር ጅግጅጋን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረ፡፡ ከ አራት ቀናት በኋላ ሁኔታው ያስፈራው ሰይድ ባሬ ፣ የሶማሊያ ሰራዊት የኢትዮጵያን ምድር ሙሉ በሙሉ ለቆ እንዲወጣ ጥሪ አስተላለፈ፡፡ ኢትዮጵያውያንም በድል ተመለሱ፡፡ በጦርነቱ ኩባ ፣ ደቡብ የመን ፣ ምስራቅ ጀርመንን የመሳሰሉ አገሮች ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የጦር ድጋፍ አድርገዋል፤ ከ 16,000 በላይ የኩባ ወታደሮችም የታሪኩ ተካፋይ ናቸው፡፡ " ታላቋ ሶማሊያም" ፈራረሰች፡፡ የዚያድባሬ የመጨረሻ ቃልም ‹‹ Nothing is permanent on this world’’ በሚል ተቋጨ፡፡ " " ክብር የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ለማስከበር ደማቸውን ላፈሰሱ የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰራዊት አባላት ። " ምንጭ ፦ Office of the Prime Minister-Ethiopia /Abiy Ahmed's Speech 💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️ ምንጭ:-....የታሪክ-ድርሳናት...የቴሌግራም ቻናል የተወሰደ ከሶማሌ ወረራ ነፃ ለማውጣት 150 ሺህ የኢትዮጵያ ወጣቶች አልቀዋል። ክብር ለጀግኖቹ ሰማዕታት!!!!💚💛❤ @timehritbebete
Mar 05, 2022