የሚገርም እና ትልቅ ጥያቄ። መልሱ ከታሰበበት ለችግራችን ውበት ያለው መፍትሔ ነው። ግን ውበት እንደታዛቢው ነውና የብዙዎቻችን መልስ ይለያል። የኔን በአጭሩ ላካፍል። ነገን ለመኖር ዛሬን ማመስገን ልልመድ። ነገን ለመኖር ዛሬ በተስፋ ልተኛ። ለነገ ሕልም ዛሬ ልተግብር፤ ለነገ ዜማ ዛሬ ልዘምር፤ ለነገ ደስታ ዛሬ ሰላምን ልፈልግ። በአጭሩ ከትላንቱ ስህተቴ ዛሬ ተምሬ ነገ የተሻለ ልሁን። ነገ ለመኖር፣ ዛሬ "ነገን ለመኖር ዛሬን ምን አድርጌ ልለፍ" ብዬ ራሴን ልጠይቅ።
Mar 04, 2022