በ ጾም ወቅት sex ማድረግ የተከለከለ ነው??? መጽሀፍ ቅዱስ ላይ ነው የሚከለክለው / ምን ላይ እንደሆነ ብትነግሩኝና ባውቅ ደስ ይለኛል thanks
Mar 03, 2022#ክፍል_2 #ጾም_እና_ሩካቤ|ግብረስጋ ግንኙነት| ከተጋባን በኋላስ ድንግልና ሳይሆን ወሲብ ቦታውን ይይዛል። በጋብቻ ወስጥ ሩካቤ |ግብረ ስጋ ግኑኝነት| በመጽሐፍ ቅዱስ እንዴት ይገለጻል ?? ዕብ 13፡4 ‹‹ መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር መኝታውም ንጹሕ ይሁን፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል››፡፡ ስለሆነም በጋብቻ ውስጥ ያለው መኝታ/ግብረ ስጋ ግኑኝነት/ ንጹሕ ነው፤ ነውር የለበትም። ይሄ ማለት ግን ባል እና ሚስት ሌላ ስራ የለባቸውም፤ ሁሌም ከአልጋ አይውረዱ ማለት አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ በሁሉ ነገራችን መመሪያ አለው… ‹‹ነገር ግን ሁሉ በአገባብና በሥርዓት ይሁን።›› 1ኛቆሮ 14፡40፡፡ ☞ ስለሆነም ሩካቤ ስጋ በቤ/ክ ገደብ ይጣልበታል ሁሌ አይፈጸምም… መቼ እንዴት ብንል? 👉 1ኛ ቆሮ 7፡4 ‹‹ ሚስት በገዛ ሥጋዋ ላይ ሥልጣን የላትም፥ ሥልጣን ለባልዋ ነው እንጂ፤ እንዲሁም ደግሞ ባል በገዛ ሥጋው ላይ ሥልጣን የለውም፥ ሥልጣን ለሚስቱ ነው እንጂ። ለጸሎት ትተጉ ዘንድ ተስማምታችሁ ለጊዜው ካልሆነ በቀር፥ እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ ፤ ራሳችሁን ስለ አለመግዛት ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ ደግሞ አብራችሁ ሁኑ።› ይሄ የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ስለ ግብረስጋ ግኑኝነት ግልጽ መመሪያ ነው። ሚስትም ባልም በገዛ ስጋቸው ስልጣን የላቸውም ስልጣኑ የትዳር አጋራቸው ነው ማለት። ባል ወይም ሚስት ከሁለት አንዳቸው ግብረ ስጋ ግኑኝነት ቢፈልጉ ሌላውን ወገን "አካሉ የኔ ነው" ብሎ መከልከል የለበትም ፤ ስልጣኑ የሱ አይደልም… ይልቁን ለትዳር አጋራችሁ ፍላጎት የነቃችሁ ሁኑ ማለት ነው… ነገር ግን ሁሌ መፈጸም አትችሉም አለ እና የማይፈጸምበት ጊዜን ሲገልጽ ‹‹ ለጸሎት ትተጉ ዘንድ ተስማምታችሁ ለጊዜው ካልሆነ በቀር፥ እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ ፤›› 1ኛ ቆሮ 7፡5፡፡ #ይቀጥላል በቀጣይ ክፍል 👉 መቼ ነው ለጸሎት የምንተጋው?
Mar 04, 2022