Matric wutete ke 700 - 540 nw ena ke egna tmrtbet kne wutet belay 37 sw ale ena campus mdeba lay sntegna bmola midersegn yimeslachual
Feb 26, 2022🔰 የ ዩኒቨርስቲ ምርጫ እንዴት እንሙላ❓ ❓ADDIS ABABA UNIVERSTIY የምመደበው ምን ባረግ ነው❓400/700 አምጥታችሁ AAU የምትመደቡበት እድል? 📊ውጤታችሁን ካያችሁ በኋላ የ ዩኒቨርስቲ ምርጫ አሞላላችሁን ከ አመጣችሁት ነጥብ ጋር በማነፃፀር ማስተካከል ለምትፈልጉ 📃 የቀሰም ቤተሰብ በ ዉስጥ መስመር የላከው መልዕክት 💡ቻLu አሁን ጊቢ ለሚመርጡ በጣም ጠቃሚ ምክር ነው። ከባለፈው አመት experienceኤ ያገኘሁትን ነው የማካፍላቸው። 📚ጊቢ በውጤት ብቻ የምትሞሉ ካላችሁ ትበላላችሁ (በተለይ የአዲስ አበባ ተማሪዎች)። ጊቢ ከመሙላታችሁ በፊት check ማድረግ ያለባችሁ ነገሮች አሉ። አለበለዚያ ግን እንደኛ 560-590 ቤት ሆናችሁ እንኳን ከ1-5 ራሱ ላይደርሳችሁ ይችላል። 💡መጀመርያና ዋናው check የምታደርጉት ነገር የትምህርት ቤታችሁን competitiveness ነው። ትምህርት ቤታችሁ በከተማው (በሀገሪቱ) ያለውን አጠቃላይ ታዋቂነት ወይም ደረጃ እና በትምህርት ቤታችሁ ምን ያህል ተማሪዎች ከናንተ በላይ ውጤት አመጡ የሚለውን ቼክ ማድረግ አለባችሁ። ይህን ለማድረግ የተለያዩ የቴሌግራም ቦቶችን መጠቀም አለባችሁ። ለምሳሌ ትምህርት ቤታችሁ የከተማው በጣም ታዋቂ ከሆነና ከናንተ በላይም የተወሰኑ ተማሪዎች በውጤት rank የሚበልጧችሁ ከሆነ፤ እመኑኝ የማትፈልጉት ቦታ የመድረስ እድላችሁ በጣም ከፍተኛ ነው። 📚ሁለተኛው ደግሞ የዩኒቨርሲቲዎችን generation ማወቅ ነው። ከ1-3 1st generation ሞልታችሁ፤ ለሰላሙ ብላችሁ ደግሞ 2nd generation በመሃል ብትቀላቅሉ፤ እዛ ጊቢ የመድረስ እድላችሁ ከ90% በላይ ነው። አይ የመጀመርያ ምርጫዬ 1st generation አይደለም የመጀመርያ ምርጫዬ 2nd generation ነው ብላችሁ ከ1-3 ብትሞሏቸው ግን በቀላሉ ታገኟችኋላችሁ። 💡ሶስተኛው ደግሞ የምትፈልጓቸው ዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ አመራረጥ ነው። ከላይ ያልኳችሁን ሁለቱን በማመዛዘን ዩኒቨርሲቲዎችን ከመረጣችሁ በኋላ፤ የነሱን የአመራረጥ rankንም ማየት ይኖርባችኋል። ለምሳሌ.... ከታዋቂ high school (ታዋቂ high school የምለው እሱ በጣም ምርጫችሁን influence ስለሚያደርግ ነው... በራሴ experience መሰረት ስላየሁት) school rank ቢያንስ 50 ሰዎች ቢበልጧችሁና እና ከ1-6 1st generation ብትሞሉ፤ የምትፈልጉትን ዩኒቨርሲቲ 1ኛ ላይ ማስቀመጥ የለባችሁም። Machineኡ የሚሰራው comprehensively ሁሉንም አይነት ምክንያቶችን ባማከለ መንገድ ስለሆነ እና ከመላው ሀገሪቱ ተማሪዎች እንዲሁም ከምትፈልጉት ዩኒቨርሲቲ የመቀበል አቅም ጋር ስለሚያስተያይ..... ማስተዋል ይኖርባችኋል። ስለዚህ ከላይ በፃፍኩት ውስጥ የምትጠቃለሉ ተማሪዎች፤ አንደኛ ምርጫችሁን ቢያንስ 3 or 4ኛ ላይ ብታደርጉት more የመድረስ እድል ይኖራችኋል። 📚ይህንን ሁሉ በቀላል ምሳሌ ለማስረዳት..... የፈለገ ውጤት ብታመጡ (ለምሳሌ 500 አናቱ ላይ) እና ከተማራችሁበት school በrank ከ1-10 ውስጥ ብትሆኑ፤ ከ1-3 ምርጫችሁ በእርግጠኝነት ይደርሳችኋል። ለዛ ነው ብዙ ተማሪዎች "እከሌ እኮ ከኔ በታች አምጥቶ/ታ አንደኛ ምርጫው/ዋ ደረሰው/ሳት" ሲሉ የሚደመጡት። ነገር ግን 570/80 አምጥታችሁ፣ በschool rank ከ10-20 ወይም ከ20 በላይ ወይም እንደየትምህርት ቤታችሁ የተማሪ ብዛ ከ50 በላይ ብትሆኑ፤ እንኳን 1ኛ ምርጫችሁ ይቅርና ከ1-3 እንኳን ላይደርሳችሁ ይችላል። ስለዚህ በኋላ ከመፀፀት፣ ምርጫችሁ ላይ smartly በደንብብብብብ እንድታስተውሉና እንድታስቡበት ከልቤ እመክራችኋለሁ። ይሄን ምክርና example የሰጠሁት ጥሩ ውጤት ላላቸው ተማሪዎች ቢሆንም፤ ሌሎቹም ተማሪዎች 3ቱን conditionኦችን ከራሳችሁ ውጤት ጋር በማስተያየት በቀላሉ ማሰብ ትችላላችሁ። 400 ቤት ሆኜ አዲስ አበባ አይደርሰኝም ማለት በድሮው የትምህርት system እንጂ ባሁኑ ዘመን አይሰራም 😊። እንደውም more chance አላችሁ እመኑኝ። ይቅናችሁ ❤️😊 ✳️ከHigh school እስከ Campus አብረናችሁ ነን ! 🔗SHARE 🔗SHARE ╔════════════╗ 📚JOIN: @QesemAcademy 📚JOIN: @QesemAcademy ╚════════════╝ ⇲
Feb 26, 2022